መዝሙር 82:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አያውቁም፥ አያስተውሉም፥ በጨለማ ውስጥ ይመላለሳሉ፥ የምድር መሠረቶች ሁሉ ተናወጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ዕውቀትም ማስተዋልም የላቸውም፤ በጨለማ ውስጥ ወዲያ ወዲህ ይመላለሳሉ፤ የምድርም መሠረቶች ሁሉ ተናወጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እነርሱ ግን ምንም አያውቁም፤ አይገባቸውምም፤ በጨለማ ይመላለሳሉ፤ በዚህም ጊዜ የምድር መሠረትዋ እየተናወጠ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአንድነት ተካክለው ተማክረዋልና፤ በአንተ ላይ ሤራ ቈረጡ፤ ቃል ኪዳንም አደረጉ፤ |
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የወይን ቦታ የእስራኤል ቤት ነው፤ የይሁዳ ሰዎችም የደስታው አትክልት ናቸው። ፍትሕን ፈለገ፤ ነገር ግን ደም ማፍሰስን አየ፤ ጽድቅን ፈለገ፤ ነገር ግን የጭንቅን ጩኸት ሰማ።
ስለዚህ ፍርድ ከእኛ ዘንድ ርቆአል፥ ጽድቅም አላገኘንም፤ ብርሃንን በተስፋ እንጠባበቅ ነበር፥ እነሆም፥ ጨለማ ሆነ፤ ጸዳልን በተስፋ እንጠባበቅ ነበር፥ ነገር ግን በጨለማ ሄድን።
ኢየሱስም “ገና ጥቂት ጊዜ ብርሃን ከእናንተ ጋር ነው። ጨለማ እንዳይደርስባችሁ ብርሃን ሳለላችሁ ተመላለሱ፤ በጨለማም የሚመላለስ ወዴት እንዲሄድ አያውቅም።
ሆኖም የእግዚአብሔር ጠንካራ መሠረት የቆመው፦ “ጌታ የራሱ የሆኑትን ያውቃል፤” እንዲሁም “የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ከዐመፅ ይራቅ፤” የሚለውን ማኅተም ታትሞ ነው።