Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -

መዝሙር 82 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም


መዝሙር 82
የአሳፍ መዝሙር።

1 እግዚአብሔር በአማልክት ጉባኤ መካከል ተሰየመ፤ በአማልክትም ላይ ይፈርዳል፤ እንዲህም ይላል፤

2 “ፍትሕን የምታጓድሉት እስከ መቼ ነው? ለክፉዎች የምታደሉትስ እስከ መቼ ነው? ሴላ

3 ለዐቅመ ቢሶችና ለድኻ አደጎች ፍረዱላቸው፤ የችግረኛውንና የምስኪኑን መብት አስከብሩ።

4 ወገን የሌለውንና ድኻውን ታደጉ፤ ከግፈኛውም እጅ አስጥሏቸው።

5 “ዕውቀትም ማስተዋልም የላቸውም፤ በጨለማ ውስጥ ወዲያ ወዲህ ይመላለሳሉ፤ የምድርም መሠረቶች ሁሉ ተናወጡ።

6 “እኔም፤ ‘እናንተ አማልክት ናችሁ፤ ሁላችሁም የልዑል ልጆች ናችሁ’ አልሁ።

7 ነገር ግን እንደ ማንኛውም ሰው ትሞታላችሁ፤ እንደ ማንኛውም ገዥ ትወድቃላችሁ።”

8 አምላክ ሆይ፤ ተነሥ፤ በምድር ላይ ፍረድ፣ ሕዝቦች ሁሉ ርስትህ ናቸውና።

መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™

የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.

በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።

The Holy Bible, New Amharic Standard Version™

Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.

Used with permission. All rights reserved worldwide. 

Biblica, Inc.
ተከተሉን:



ማስታወቂያዎች