Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -

መዝሙር 14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)


1 ለመዘምራን አለቃ፥ የዳዊት መዝሙር።

1 ለመዘምራን አለቃ፥ የዳዊት መዝሙር። አላዋቂ በልቡ፦ አምላክ የለም ይላል። በሥራቸው ረከሱ፥ ጐሰቈሉ፥ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም።

2 የሚያስተውል እግዚአብሔርንም? የሚፈልግ እንዳለ ያይ ዘንድ ጌታ ከሰማይ የሰው ልጆችን ተመለከተ።

3 ሁሉም ዐመፁ በአንድነትም ረከሱ፥ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም፥ አንድም እንኳ የለም።

4 ክፉ አድራጊዎች አያስተውሉምን? እንጀራን እንደሚበሉ ሕዝቤን የሚያኝኩ፥ ጌታን አይጠሩምን፥

5 እዚያም ታላቅ ፍርሃት ይዞአቸዋል፥ አግዚአብሔር በጻድቃን ዘንድ ነውና፥

6 የምስኪኖችን ዕቅድ ታዛባላችሁ፥ ጌታ ግን መጠለያቸው ነው፥

7 ከጽዮን መድኃኒትን ለእስራኤል ማን ይሰጣል? ጌታ የሕዝቡን ምርኮ በመለሰ ጊዜ፥ ያዕቆብ ደስ ይለዋል፥ እስራኤልም ሐሤት ያደርጋል።

ተከተሉን:



ማስታወቂያዎች