Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢሳይያስ 5:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የወይን ቦታ የእስራኤል ቤት ነው፤ የይሁዳ ሰዎችም የደስታው አትክልት ናቸው። ፍትሕን ፈለገ፤ ነገር ግን ደም ማፍሰስን አየ፤ ጽድቅን ፈለገ፤ ነገር ግን የጭንቅን ጩኸት ሰማ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 የሰራዊት ጌታ የእግዚአብሔር የወይን ቦታው የእስራኤል ቤት ነው፤ የይሁዳ ሰዎችም የደስታው አትክልት ናቸው። ፍትሕን ፈለገ፤ ነገር ግን ደም ማፍሰስን አየ፤ ጽድቅን ፈለገ፤ ነገር ግን የጭንቅን ጩኸት ሰማ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ይህም የሠራዊት አምላክ የወይን ቦታ የተባለው የእስራኤል ሕዝብ ነው፤ እርሱም የይሁዳ ሕዝብ ደስ የሚሰኝበት ተክል ነው። መልካም ሥራ እንዲሠሩ ተስፋ ያደርግ ነበር፤ በዚህ ፈንታ ነፍሰ ገዳዮች ሆኑ፤ ቅን ፍርድ ይሰጣሉ ብሎ ተስፋ ያደርግ ነበር፤ እነርሱ ግን ፍርድን በማጓደላቸው የሕዝቡ ጩኸት በዛ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 የሠ​ራ​ዊት ጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወይን ቦታ እርሱ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ነው፤ ተወ​ዳጁ አዲስ ተክ​ልም የይ​ሁዳ ሰዎች ናቸው፤ ፍር​ድን ያደ​ር​ጋል ብየ እጠ​ብቅ ነበር፤ እነ​ሆም፥ ዐመ​ፅን አደ​ረገ፤ ጽድ​ቅ​ንም አይ​ደ​ለም፥ ጩኸ​ትን እንጂ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ወይን ቦታ እርሱ የእስራኤል ቤት ነው፥ የደስታውም አትክልት የይሁዳ ሰዎች ናቸው፥ ፍርድን ተስፋ ያደርግ ነበር፥ እነሆም፥ ደም ማፍሰስ ሆነ፥ ጽድቅንም ይተማመን ነበር፥ እነሆም፥ ጩኸት ሆነ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢሳይያስ 5:7
47 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ጌታም ቃየልን እንዲህ አለው፥ “ምን አደረግህ? የወንድምህ የደሙ ድምፅ ከምድር ወደ እኔ ይጮኻል።


የራሱ የሆነ መኖሪያ እንዲኖረውና ከእንግዲህ ወዲያ እንዳይናወጥ፥ ለሕዝቤ ለእስራኤል ቦታ እሰጠዋለሁ፤ አጸናዋለሁም። ከእንግዲህ ወዲህ ክፉ ሕዝብ አይጨቁነውም፤ ከዚህ በፊት እንደ ሆነው፥


ጌታ በሚፈሩት፥ በጽኑ ፍቅሩ በሚታመኑት ይደሰታል።


ጌታ በሕዝቡ ተደስቶአልና፥ የዋሃንንም በማዳኑ ያስጌጣቸዋል።


የሠራዊት አምላክ ሆይ፥ እንግዲህ ተመለስ፥ ከሰማይ ተመልከት፥ እይም፥ ይህችንም የወይን ግንድ ጐብኝ።


ጌታም አለ፦ “በግብጽ ያለውን የሕዝቤን መከራ በእውነት አየሁ፥ በአስገባሪዎቻቸውም ምክንያት የሚጮሁትን ጩኸት ሰማሁ፤ ሥቃያቸውንም አውቄአለሁ።


የድሀውን ጩኸት እንዳይሰማ ጆሮውን የሚደፍን ሰው፥ እርሱ ራሱ ይጮኻል አይሰማለትምም።


እኔም ተመለስሁ፥ ከፀሐይ በታችም የሚደረገውን ግፍ ሁሉ አየሁ፥ እነሆም፥ የተገፉት ሰዎች እንባ፥ የሚያጽናናቸውም አልነበረም፥ በሚገፉአቸውም እጅ ኃይል ነበረ፥ እነርሱን ግን የሚያጽናናቸው አልነበረም።


ፍቅር ሆይ፥ እንዴት የተዋብሽ ነሽ! እንዴትስ ደስ ታሰኛለሽ! በተድላ


ታማኝ የነበረችው ከተማ እንዴት አመንዝራ እንደ ሆነች ተመልከቱ! ቀድሞ ፍትሕ የሞላባት፤ ጽድቅ የሰፈነባት ነበረች፤ አሁን ግን የነፍሰ ገዳዮች ማደሪያ ሆነች!


ከእግር ጥፍራችሁ እስከ ራስ ጠጉራችሁ ጤና የላችሁም፤ ቁስልና ዕባጭ እንዲሁም እዥ ብቻ ነው፤ አልታጠበም፤ አልታሰረም፤ በዘይትም አልለዘበም።


በዚያም ቀን ለተወደደው የወይን ቦታ ተቀኙለት።


ጌታ ከአለቆችና ከሕዝቡ ሽማግሌዎች ጋር እንዲህ ሲል ይፋረዳል፤ “የወይኔን ቦታ ያጠፋችሁ እናንተ ናችሁ፤ ከድኾች የዘረፋችሁትም በቤታችሁ ይገኛል፤


ሕዝቤን በችግር ስታደቁት፤ የድኾችንም ፊት በኀዘን ስታገረጡት ምን ማለታችሁ ነው?” ይላል ጌታ፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


ስለዚህ፤ ጌታ በጽዮን ሴቶች ዐናት ላይ ቆረቆር ያመጣል፤ ጌታም ራሳቸውን ቡሀ ያደርጋል።


ስለዚህ የእስራኤል ቅዱስ እንዲህ ይላል፦ ይህችን ቃል አቃልላችኋልና፥ በግፍና በጠማምነት ታምናችኋልና፥ በእርሱም ተደግፋችኋልና፥


እናንተ ከጽድቅ የራቃችሁ እልከኞች፥ ስሙኝ፤


መሬቱን ቈፈረ፤ድንጋይንም ለቅሞ አወጣ፤ ምርጥ የሆነውንም ወይን ተከለበት። በመካከሉ መጠበቂያ ማማ ሠራ፤ የወይን መጭመቂያ ጉድጓድም አበጀ፤ ከዚያ መልካም ፍሬ ያፈራል ብሎ አሰበ፤ ነገር ግን ኮምጣጣ ፍሬ አፈራ።


ዐምፀናል፥ ሐሰትን ተናግረናል፥ ጌታን ከመከተል ተመልሰናል፤ ግፍንና ዓመፅንም ተናግረናል፥ የኃጢአት ቃልንም ፀንሰን ከልብ አውጥተናል።


ፍትህም ወደ ኋላ ተመልሶአል፥ ጽድቅም በሩቅ ቆሞአል፤ እውነትም በአደባባይ ላይ ወድቆአልና፥ ቅንነትም ሊገባ አልቻለም።


በጽድቅ የሚጠራ በእውነትም የሚፈርድ የለም፤ በእርባና ቢስ ነገር ታምነዋል ሐሰትንም ተናግረዋል፤ ጉዳትን ፀንሰዋል በደልንም ወልደዋል።


ጎልማሳም ድንግሊቱን እንደሚያገባ፥ እንዲሁ ልጆችሽ ያገቡሻል፤ ሙሽራም በሙሽራይቱ ደስ እንደሚለው፥ እንዲሁ አምላክሽ በአንቺ ደስ ይለዋል።


ብዙ እረኞች የወይኑን ቦታዬን አጥፍተዋል፥ እድል ፈንታዬንም ረግጠዋል፤ የአምሮቴን እድል ፈንታ ምድረ በዳ አድርገውታል።


በአንደኛው ቅርጫት አስቀድሞ እንደ ደረሰ በለስ የሚመስል እጅግ መልካም በለስ ነበረበት፤ በሁለተኛውም ቅርጫት ከክፋቱ የተነሣ ሊበላ የማይችል እጅግ ክፉ በለስ ነበረበት።


ባቢሎን ስትያዝ ከነበረው የሁካታ ድምፅ የተነሣ ምድር ተናወጠች፥ ጩኸትም በአሕዛብ መካከል ተሰማ።


የምድሪቱ ሕዝብ ግፍ አደረጉ፥ ዝርፊያም ፈፀሙ፥ ድሃውንና ችግረኛውን አንገላቱ፥ መጻተኛውንም ያለ ፍትሕ በደሉ።


እስራኤል ፍሬውን የሚሰጥ የተትረፈረፈ ወይን ነው፤ እንደ ፍሬው ብዛት መሠዊያዎችን አብዝቶአል፤ እንደ ምድሩም ብልጥግና መጠን ሐውልቶችን እያሳመሩ ሠርተዋል።


ባለ ጠጎችዋ ግፍ ተሞልተዋል፤ በውስጧ የሚኖሩትም ሐሰት ተናግረዋል፥ ምላሳቸውም በአፋቸው ውስጥ አታላይ ነው።


ሰው ሆይ፥ መልካም ምን እንደሆነ ለአንተ ነግሮሃል፤ ፍትሕን እንድታደርግ፥ ምሕረትን እንድትወድና ከአምላክህም ጋር በትሕትና እንድትሄድ ካልሆነ በቀር ጌታ ከአንተ የሚፈልገው ምንድነው?


ክፉ ሥራ ለምን አሳየኸኝ? ድካምንስ ለምን ትመለከታለህ? ጥፋትና ግፍ በፊቴ ነው፤ ጠብና ክርክር ይነሣሉ።


ጌታ አምላክሽ በመካከልሽ ኃያል ታዳጊ ነው፤ በአንቺም በፍጹም በደስታ ደስ ይለዋል፥ በፍቅሩም ያርፋል፥ በእልልታም በአንቺ ደስ ይለዋል።”


“እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን!ወዮላችሁ፥ ምክንያቱም ከአዝሙድ፥ ከእንስላልና ከከሙን አሥራት ታወጣላችሁ፥ በሕግ ያለውን ዋና ነገር ፍርድን፥ ምሕረትንና እምነትን ትተዋላችሁ፤ ሌላውን ሳትተዉ እነዚህን ልታደርጉ ይገባችሁ ነበር።


እግዚአብሔር ታዲያ ቀንና ሌሊት ወደ እርሱ ለሚጮኹ፥ ለሚታገሣቸውም ምርጦቹ አይፈርድላቸውምን?


በእኔ ያለውን ፍሬ የማያፈራውን ቅርንጫፍ ሁሉ ያስወግደዋል፤ ፍሬ የሚያፈራውንም ሁሉ አብዝቶ እንዲያፈራ ያጠራዋል።


‘ዕዳ የሚሠረዝበት ሰባተኛው ዓመት ተቃርቧል’ የሚል ክፉ ሐሳብ አድሮብህ፥ በችግረኛ ወንድምህ ላይ እንዳትጨክንና ምንም ሳትሰጠው እንዳትቀር፥ እርሱም በአንተ ላይ ወደ ጌታ ጮኾ በደለኛ እንዳትሆን ተጠንቀቅ!


እነሆ፥ እርሻችሁን ሲያጭዱ ለዋሉ ሠራተኞች ያልከፈላችሁት ደመወዝ በእናንተ ላይ ይጮኻል፤ የአጫጆቹም ጩኸት የሠራዊት ጌታ ጆሮ ደርሶአል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች