መዝሙር 47:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሕዛብን ከእኛ በታች፥ ወገኖችንም ከእግራችን በታች አስገዛልን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለሚወድደው ለያዕቆብ ክብር የሆነችውን፣ ርስታችንን እርሱ መረጠልን። ሴላ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ርስት አድርገን የምንይዛትን ምድር መረጠልን፤ ይህችም ምድር ለሚወድደው ለእስራኤል ሕዝብ መመኪያ ናት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆ፥ የምድር ነገሥታት ተሰብስበው በአንድነት መጥተዋል። |
እኔ ግን፦ “‘ከወንዶች ልጆች ጋር እንዴት አስቀምጥሻለሁ? ያማረችውንስ ምድር እጅግ የከበረችውን የአሕዛብን ርስት እንዴት እሰጥሻለሁ? ብዬ ነበር። ደግሞ፦ አባቴ ብለሽ ትጠሪኛለሽ፤ እኔንም ከመከተል አትመለሽም ብዬ ነበር።
አሦር አያድነንም፤ በፈረስ ላይ አንቀመጥም፤ ድሀ አደጉም በአንተ ዘንድ ምሕረትን ያገኛልና ከእንግዲህ ወዲህ ለእጆቻችን ሥራ፦ ‘አምላኮቻችን’ ናችሁ አንላቸውም።”
ጌታ እግዚአብሔር፦ “የያዕቆብን ትዕቢት ተጸይፌአለሁ፥ የንጉሥ ቅጥሮቹንም ጠልቻለሁ፤ ስለዚህ ከተማይቱንና በውስጧ ያለውን ሁሉ አሳልፌ እሰጣለሁ” ብሎ በራሱ ምሎአል፥ ይላል ጌታ የሠራዊት አምላክ።
ወድጃችኋለሁ ይላል ጌታ፤ እናንተ ግን፦ “እንዴት ወደድከን?” ትላላችሁ። ዔሳው የያዕቆብ ወንድም አልነበረምን? ይላል ጌታ። ሆኖም ያዕቆብን ወደድኩት።
በእርሱ የተጠራችሁበት ተስፋ ምን እንደሆን፥ ከቅዱሳንም ጋር የሚኖራችሁን የርስት ክብር ባለጠግነት ምንነት እንድታውቁ፥ የልቦናችሁ ዐይኖች እንዲበሩ፤