Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 3:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 እኔ ግን፦ “‘ከወንዶች ልጆች ጋር እንዴት አስቀምጥሻለሁ? ያማረችውንስ ምድር እጅግ የከበረችውን የአሕዛብን ርስት እንዴት እሰጥሻለሁ? ብዬ ነበር። ደግሞ፦ አባቴ ብለሽ ትጠሪኛለሽ፤ እኔንም ከመከተል አትመለሽም ብዬ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 “እኔም፣ “ ‘የተመረጠችውን ምድር፣ የትኛውም ሕዝብ ያላገኘውን የተዋበች ርስት ልሰጥሽ፣ እንደ ወንዶች ልጆቼ ምንኛ በደስታ ልቍጠርሽ’ አልሁ፤ ‘አባቴ’ ብለሽ የምትጠሪኝ፣ እኔንም ከመከተል ዘወር የማትዪ መስሎኝ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እስራኤል ሆይ! አንቺን እንደ ልጅ አድርጌ በመቀበል፥ ከዓለም እጅግ የተዋበችውንና ለም የሆነችውን ምድር ልሰጥሽ ፈለግኹ፤ ‘አባት’ ብለሽ እንድትጠሪኝና ዳግመኛ ከእኔ እንዳትርቂ በመጠበቅ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 “እኔም፦ ይሁን አልሁ፤ በወ​ን​ዶች ልጆች መካ​ከል እሾ​ም​ሃ​ለሁ፤ አሕ​ዛ​ብን የሚ​ገዛ ሁሉን ቻይ የሆነ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ርስት የተ​መ​ረ​ጠ​ች​ውን ምድር ለአ​ንተ እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ፤ አባቴ ትለ​ኛ​ለህ፤ ከእ​ኔም አት​መ​ለ​ስም አልሁ ብለ​ሃ​ልና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 እኔ ግን፦ ከወንዶች ልጆች ጋር እንዴት አደርግሻለሁ? ያማረችውንስ ምድር የከበረችውን የአሕዛብን ሠራዊት ርስት እንዴት እሰጥሻለሁ? ብዬ ነበር። ደግሞ፦ አባቴ ብለሽ ትጠሪኛለሽ እኔንም ከመከተል አትመለሽም ብዬ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 3:19
32 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አሁን፦ ‘አንተ አባቴ ሆይ፥ የብላቴንነቴ ወዳጅ ነህ’ ብለሽ አልጠራሽኝምን?


በልቅሶ ይወጣሉ፤ እኔንም በመማፀናቸው እየመራሁ እመልሳቸዋለሁ፤ በወንዝ ዳር በቅን መንገድ አስኬዳቸዋለሁ፤ በእርሱም አይሰናከሉም፤ እኔ ለእስራኤል አባት ነኝና፥ ኤፍሬምም በኩሬ ነውና።


አብርሃም ባያውቀን፥ እስራኤልም ባይገነዘበን አንተ አባታችን ነህ፤ አቤቱ ጌታ አንተ አባታችን ነህ፤ ስምህም ከዘለዓለም ታዳጊያችን ነው።


እኛ ግን ነፍሳቸውን ሊያድኑ ከሚያምኑት ጋር ነን እንጂ፥ ወደ ጥፋት ከሚያፈገፍጉ ጋር አይደለንም።


በበጎ ፈቃዱ እንደ ወደደ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ልጆቹ እንድንሆን አስቀድሞ ወሰነን።


በክርስቶስ ኢየሱስ ባላችሁ እምነት ሁላችሁ የእግዚአብሔር ልጆች ናችሁና፤


ኤፍሬም ሆይ! እንዴት እጥልሃለሁ? እስራኤል ሆይ! እንዴትስ አሳልፌ እሰጥሃለሁ? እንዴትስ እንደ አድማህ አደርግሃለሁ? እንዴትስ እንደ ጲቦይም እመለከትሃለሁ? ልቤ በውስጤ ተናውጣለች፥ ምሕረቴም ተነሣሥታለች።


በዚያ ቀን ከግብጽ ምድር ወዳዘጋጀሁላችሁ፥ ወተትና ማር ወደምታፈስሰው፥ የምድርም ሁሉ ጌጥ ወደምትሆን ምድር አወጣቸው ዘንድ ማልሁላቸው።


በእውነት ኤፍሬም የተወደደ ልጄ ነውን? ወይስ ደስ የምሰኝበት ሕፃን ነውን? በእርሱ ላይ በተናገርሁ ቍጥር አሁንም ድረስ በትክክል አስታውሰዋለሁ፤ ስለዚህ አንጀቴ ታወከችለት ርኅራኄም እራራለታለሁ፥ ይላል ጌታ።


ብዙ እረኞች የወይኑን ቦታዬን አጥፍተዋል፥ እድል ፈንታዬንም ረግጠዋል፤ የአምሮቴን እድል ፈንታ ምድረ በዳ አድርገውታል።


“በእነዚህ ነገሮች ይቅር የምልሽ እንዴት አድርጌ ነው? ልጆችሽ ትተውኛል፥ አማልክትም ባልሆኑ ምለዋል፤ ካጠገብኋቸውም በኋላ አመነዘሩ በጋለሞቶቹም ቤት ተሰበሰቡ።


አሁን ግን፥ አቤቱ ጌታ፥ አንተ አባታችን ነህ፤ እኛ ጭቃ ነን፤ አንተም ሠሪያችን ነህ፥ እኛም ሁላችን የእጅህ ሥራ ነን።


ጠቢባን ክብርን ይወርሳሉ፥ ሞኞች ግን መዋረድን ይቀበላሉ።


የምትወደደውን ምድር ናቁ፥ በቃሉም አልታመኑም፥


ለሰው ፊትም ሳያደላ በእያንዳንዱ ላይ እንደ ሥራው የሚፈርደውን አባት ብላችሁ የምትጠሩት ከሆነ፥ በእንግድነታችሁ ዘመን በፍርሃት ኑሩ።


ገመድ ባማረ ስፍራ ወደቀችልኝ፥ ርስቴም ተዋበችልኝ።


እጁን በባሕር ላይ ቀኙንም በወንዞች ላይ አኖራለሁ።


በዚያም ዘመን ኢየሩሳሌምን የጌታ ዙፋን ብለው ይጠሩአታል፥ በጌታ ስም አሕዛብም ሁሉ ወደ እርሷ ወደ ኢየሩሳሌም ይሰበሰባሉ፤ ከእንግዲህም ወዲህ ክፉውን እልኸኛ ልባቸውን ተከትለው አይሄዱም።


የምሠራላቸውንም በጎነት ሁሉ በሚሰሙ የምድር አሕዛብ ሁሉ ፊት ይህች ከተማ ለእኔ የምስጋናና የክብር የደስታም ስም ትሆናለች፤ እኔም ስላደረግሁላት በጎነትና ሰላም ሁሉ ይፈራሉ ይንቀጠቀጣሉም።


“እናንተ የጌታ የእግዚአብሔር ልጆች ናችሁ፤ ለሞተ ሰው ሰውነታችሁን አትቦጭቁ፤ የጭንቅላታችሁን ጠጉር አትላጩ፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች