ኢሳይያስ 60:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)15 ከሰውም ማንም እስከማያልፍብሽ ድረስ የተተውሽና የተጠላሽ ነበርሽ፤ ነገር ግን የዘለዓለም ትምክሕትና የልጅ ልጅ ደስታ አደርግሻለሁ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም15 “የተተውሽና የተጠላሽ፣ ማንም ሰው የማያልፍብሽ ብትሆኝም እንኳ፣ እኔ የዘላለም ትምክሕት፣ የትውልድም ሁሉ ደስታ አደርግሻለሁ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም15 “ከዚህ በፊት የተተውሽና የተጠላሽ ሆነሽ ማንም በአንቺ በኩል የማያልፍ የነበረ ቢሆንም እንኳ፥ የዘለዓለም መመኪያና በየትውልዱ ሁሉ መደሰቻ እንድትሆኚ አደርግሻለሁ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)15 የተተውሽና የተጠላሽ ሆነሻልና የሚረዳሽ አጣሽ፤ ነገር ግን የዘለዓለም ደስታን ለልጅ ልጅ እሰጥሻለሁ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)15 ከሰውም ማንም እስከማያልፍብሽ ድረስ የተተውሽና የተጠላሽ ነበርሽ፥ ነገር ግን የዘላለም ትምክሕትና የልጅ ልጅ ደስታ አደርግሻለሁ። ምዕራፉን ተመልከት |