መዝሙር 2:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ተግሣጹን ተቀበሉ ጌታ እንዳይቈጣ እናንተም በመንገድ እንዳትጠፉ፥ ቁጣው ፈጥና ትነድዳለችና። በእርሱ የታመኑ ሁሉ የተመሰገኑ ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዳይቈጣና በመንገድ እንዳትጠፉ፣ ዝቅ ብላችሁ ልጁን ሳሙት፤ ቍጣው ፈጥኖ ይነድዳልና። እርሱን መጠጊያ የሚያደርጉ ሁሉ ብፁዓን ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቊጣው በቅጽበት ስለሚነድ በእናንተ ላይ ተቈጥቶ እንዳያጠፋችሁ በመንቀጥቀጥ ስገዱለት እርሱን መጠጊያ የሚያደርጉ ሁሉ የተባረኩ ናቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጥበብን አጽኑአት፤ እግዚአብሔር እንዳይቈጣ፥ እናንተም ከጽድቅ መንገድ እንዳትጠፉ፥ ቍጣው ፈጥና በነደደች ጊዜ፥ በእርሱ የታመኑ ሁሉ ብፁዓን ናቸው። |
ይሁን እንጂ ለእኔ ታማኞች የሆኑ፥ ለባዓል ያልሰገዱና ምስሉንም ያልተሳለሙ ሰባት ሺህ ሰዎችን በእስራኤል ምድር በሕይወት እንዲተርፉ አደርጋለሁ።”
ጌታም የፍርድ አምላክ ነው፤ ስለ ሆነም ጌታ ይራራላችኋልና ይታገሣል፤ ሊምራችሁም ከፍ ከፍ ይላል፤ እርሱን በመተማመን የሚጠባበቁ ሁሉ ብፁዓን ናቸው።
አሁንም ኃጢአትን እጅግ አብዝተው ይሠራሉ፤ በብራቸውም ለራሳቸው ቀልጦ የተሠራ ምስልን፥ እንደ ጥበባቸውም ጣዖታትን ሠርተዋል፤ ሁሉም የሞያተኞች ሥራ ናቸው። ስለ እነርሱም የሚሠዉ ሰዎች፦ “እምቦሳውን ይሳሙ” ይላሉ።
ከዚያም ሳሙኤል የዘይቱን ብርሌ ወስዶ፥ ዘይቱን በሳኦል ራስ ላይ ካፈሰሰ በኋላ ሳመው፥ እንዲህም አለው፤ “በርስቱ ላይ ገዥ ትሆን ዘንድ ጌታ ቀብቶህ የለምን?