Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 31:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 በአንተ ለሚያምኑ በሰው ልጆች ፊት ያዘጋጀሃት ለሚፈሩህም የሰወርሃት፥ ቸርነትህ እንደምን በዛች!

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ከሰዎች ሤራ፣ በማደሪያህ ውስጥ ትሸሽጋቸዋለህ፤ ከአንደበት ጭቅጭቅም፣ በድንኳንህ ውስጥ ትከልላቸዋለህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ከሚያሤሩባቸው ሰዎች በመኖሪያህ ጥላ ሥር ትደብቃቸዋለህ፤ ከመርዘኛ አንደበትም በከለላህ ትጠብቃቸዋለህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 31:20
27 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በመከራ ቀን በድንኳኑ ሰውሮኛልና፥ በድንኳኑም መሸሸጊያ ሸሽጎኛልና፥ በዓለት ላይ ከፍ ከፍ አድርጎኛልና።


አንተ ለእኔ መሸሸጊያዬ ነህ፥ ከጭንቅ ትጠብቀኛለህ፥ ከከበቡኝ ታድነኝ ዘንድ ደስታዬ ነህ።


ከምላስ ጅራፍ ትሰወራለህ፥ የጥፋት አደጋ ሲመጣም አትፈራም።


አቤቱ፥ ከክፉዎች እጅ ጠብቀኝ፥ እርምጃዬንም ሊያሰናክሉ ከመከሩ ከዓመፀኞች አድነኝ።


በልባቸውም ክፉ ካሰቡ፥ ቀኑን ሁሉ ለሰልፍ ከሚከማቹ።


አዲስ ዝማሬን ለአምላካችን ምስጋና በአፌ ጨመረ፥ ብዙዎች ያያሉ ይፈሩማል፥ በጌታም ይታመናሉ።


በክፉዎች ትዕቢት ምስኪኖች ይሰደዳሉ፥ ባሰቡት ተንኰላቸው ተጠመዱ።


በትዕቢት ባደረጉባቸው ነገር ላይ ጌታ ከአማልክት ሁሉ እንደሚበልጥ አሁን አወቅሁ።”


ስለዚህ፥ “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል” እንደሚል፥ የሚሰጠው ጸጋ ግን ከሁሉም ይበልጣል።


በትዕቢት የተወጠረና ምንም የማያውቅ ነው፤ ነገር ግን የንትርክና በቃላት የመከራከር ለየት ያለ ክፉ ምኞት አለበት፤ እነዚህም ነገሮች የሚያመጡት ቅንዓትን፥ መከፋፈልን፥ ስድብን፥ ክፉ ጥርጣሬን፥


ጽኑ ፍቅርህን በሚያውቁህ ላይ፥ ጽድቅህንም ልባቸው በቀና ላይ ዘርጋ።


ወደ እናንት ስመጣ፥ እኔ እንደምፈልገው ሆናችሁ ላላገኛችሁ እችላለሁ ወይም እናንተ እንደምትፈልጉኝ ሆኜ ላታገኙኝ ትችላላችሁ ብዬ እፈራለሁ፤ ምናልባት ክርክር፥ ቅንዓት፥ ቁጣ፥ አድመኝነት፥ ሐሜት፥ ማሾክሾክ፥ ኩራት፥ ሁከትም ይኖር ይሆን ብዬ እሰጋለሁ።


በቀን እንደምንሆነው በጨዋነት እንመላለስ፤ በመሶልሶልና በስካር አይሁን፤ በዝሙትና በመዳራት አይሁን፤ በክርክርና በቅናት አይሁን፤


በዚያን ጊዜ የጐርፍ ውኃ በነፍሳችን ላይ ባለፈ ነበር።


ጣዖትን ማምለክ፥ አስማት፥ ጠላትነት፥ ጠብ፥ ቅናት፥ ቁጣ፥ አድመኛነት፥ መለያየት፥ መናፍቅነት፥


አቤቱ፥ ትዕቢተኞች በእኔ ላይ ተነሥተዋል፥ የክፉዎችም ማኅበር ነፍሴን ፈለጉአት፥ ላንተም ምንም ቦታ የላቸውም።


ተግሣጹን ተቀበሉ ጌታ እንዳይቈጣ እናንተም በመንገድ እንዳትጠፉ፥ ቁጣው ፈጥና ትነድዳለችና። በእርሱ የታመኑ ሁሉ የተመሰገኑ ናቸው።


አቤቱ፥ ጽኑ ፍቅርህ በሰማይ ነው፥ ታማኝነትህም ወደ ደመናት ትደርሳለች።


አቤቱ፥ ጽኑ ፍቅርህን እንዴት አበዛህ! የሰው ልጆች በክንፎችህ ጥላ ይታመናሉ።


ርኅራኄህ እስከ ሰማይ ድረስ ከፍ ብላለችና፥ እውነትህም እስከ ደመናት ድረስ።


ጌታ ርኅሩኅና ቸር ነው፥ ከቁጣ የራቀ ፍቅሩም የበዛ።


ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል፥ እንዲሁ ምሕረቱን በሚፈሩት ላይ አጠነከረ።


ለባርያህ እንደ ምሕረትህ አድርግ፥ ሥርዓትህንም አስተምረኝ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች