Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኢሳይያስ 30:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ጌታም የፍርድ አምላክ ነው፤ ስለ ሆነም ጌታ ይራራላችኋልና ይታገሣል፤ ሊምራችሁም ከፍ ከፍ ይላል፤ እርሱን በመተማመን የሚጠባበቁ ሁሉ ብፁዓን ናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 እግዚአብሔር ግን ምሕረት ሊያደርግላችሁ ይታገሣል፤ ርኅራኄም ሊያሳያችሁ ይነሣል። እግዚአብሔር የፍትሕ አምላክ ነውና፣ እርሱን በመተማመን የሚጠባበቁት ብፁዓን ናቸው!

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ይህም ሁሉ ሆኖ እግዚአብሔር ምሕረት ሊያደርግላችሁ ተዘጋጅቶአል፤ እግዚአብሔር የፍትሕ አምላክ ስለ ሆነ ሊራራላችሁ ወዶአል፤ ስለዚህ በእግዚአብሔር የሚታመኑ ሁሉ የተባረኩ ናቸው።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፈራጅ ነውና ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይራ​ራ​ላ​ችሁ ዘንድ ይታ​ገ​ሣል፤ ይም​ራ​ች​ሁም ዘንድ ከፍ ከፍ ይላል፤ እር​ሱን በመ​ተ​ማ​መን የሚ​ጠ​ባ​በቁ ሁሉ ብፁ​ዓን ናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 እግዚአብሔርም የፍርድ አምላክ ነውና ስለዚህ እግዚአብሔር ይራራላችሁ ዘንድ ይታገሣል፥ ይምራችሁም ዘንድ ከፍ ከፍ ይላል፥ እርሱን በመተማመን የሚጠባበቁ ሁሉ ብፁዓን ናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢሳይያስ 30:18
69 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አንዳንዶች የሚዘገይ እንደሚመስላቸው፥ ጌታ ስለ ተስፋ ቃሉ አይዘገይም፤ ነገር ግን ሰው ሁሉ ለንስሓ እንዲበቃና ማንም እንዳይጠፋ ወዶ ስለ እናንተ ይታገሣል።


ቃልን የሚያዳምጥ መልካም ነገርን ያገኛል፥ በጌታ የታመነ ምስጉን ነው።


ፊቱን ከያዕቆብ ቤት የሸሸገውን ጌታን እጠብቃለሁ፤ እርሱንም ተስፋ አደርጋለሁ።


በዚያም ቀን፦ እነሆ፥ አምላካችን ይህ ነው፤ ተስፋ አድርገነዋል፥ ያድነንማል፤ ጌታ ይህ ነው፤ ጠብቀነዋል፤ በማዳኑ ደስ ይለናል፤ ሐሤትም እናደርጋለን፥ ይባላል።


የጌታ መልአክ ጌታን በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል፥ ያድናቸውማል።


የጌታችንም ትዕግሥት ለእናንተ መዳን እንደሆነ ቁጠሩ። እንደዚሁ የተወደደው ወንድማችን ጳውሎስ እንደተሰጠው ጥበብ መጠን ጻፈላችሁ፤


ተነሥቶም ወደ አባቱ መጣ። እርሱም ገና ሩቅ ሳለ አባቱ አየውና አዘነለት፤ ሮጦም አንገቱን አቀፈውና ሳመው።


አሳቤ እንደ አሳባችሁ መንገዳችሁም እንደ መንገዴ አይደለምና፥ ይላል ጌታ።


በጌታ ተስፋ አድርግ፥ በርታ፥ ልብህም ይጽና፥ በጌታ ተስፋ አድርግ።


ጌታም በአርያም ተቀምጦአልና ከፍ ከፍ አለ፤ ጽዮንን በፍትህና በጽድቅ ሞላት።


ነገር ግን እግዚአብሔር ቁጣውን ለማሳየትና ኃይሉን ለማሳወቅ ፈልጎ፥ ለጥፋት የተዘጋጁትን የቁጣ ዕቃዎችን በብዙ ትዕግሥት ተቋቁሞ ቢሆንስ?


በጌታ የታመነ ጌታም መተማመኛው የሆነ ሰው ቡሩክ ነው።


በትዕግሥት የጸኑትን የተባረኩ አድርገን እንደምንቈጥር ታውቃላችሁ፤ ኢዮብ እንዴት ታግሦ እንደ ጸና ሰምታችኋል፤ ጌታም በመጨረሻ ያደረገለትን አይታችኋል። ጌታ እጅግ ርኅሩኅና መሓሪ ነው።


የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ግን በፍትሕ ከፍ ከፍ ይላል፤ ቅዱሱም አምላክ ቅድስናውን በጽድቅ ይገልጻል።


እጅግ በመኩራራት አትናገሩ፥ የእብሪትም ቃል ከአፋችሁ አይውጣ፥ ጌታ አምላክ አዋቂ ነውና፥ በእርሱም ሥራዎች ይመዘናሉ።


ጸጋውንም አበዛልን። በጥበብና በአእምሮ ሁሉ፥


በደል እንዲበዛ ሕግ ገባ፤ ነገር ግን ኃጢአት በበዛበት፥ ጸጋ ይበልጥ በዛ፤


ይህን እግዚአብሔር፥ ለእስራኤል ንስሐን የኃጢአትንም ስርየት እንዲሰጥ፥ ራስም መድኃኒትም አድርጎ በቀኙ ከፍ ከፍ አደረገው።


እነሆም፥ በኢየሩሳሌም ስምዖን የሚባል አንድ ሰው ነበረ፤ ይህም ሰው የእስራኤልን መጽናናት የሚጠብቅ፥ ጻድቅና ትጉህም ነበረ፤ መንፈስ ቅዱስም በእርሱ ላይ ነበረ።


በቃላችሁ ጌታን አሰልችታችሁታል። እናንተም፦ እርሱን ያሰለቸነው በምንድን ነው? ትላላችሁ። “ክፉን የሚያደርግ ሁሉ በጌታ ፊት መልካም ነው፥ እርሱም በእነርሱ ደስ ይለዋል” ወይም “የፍትሕ አምላክ የት አለ?” በማለታችሁ ነው።


ተግሣጹን ተቀበሉ ጌታ እንዳይቈጣ እናንተም በመንገድ እንዳትጠፉ፥ ቁጣው ፈጥና ትነድዳለችና። በእርሱ የታመኑ ሁሉ የተመሰገኑ ናቸው።


ጌታም በፊቱ አልፎ እንዲህ ብሎ አወጀ፦ “ጌታ፥ ጌታ፥ መሓሪ አምላክ፥ ሞገስ ያለው፥ ታጋሽ፥ ፅኑ ፍቅሩና እውነቱ የበዛ፥


በውድ ልጁም በነጻ የሰጠን የከበረ ጸጋው እንዲመሰገን ይህን አደረገ።


በደላቸውንም ተቀብለው ፊቴን እስኪሹ ድረስ ወደ ስፍራዬ ተመልሼ እሄዳለሁ፤ በመከራቸው ጊዜ እጅግ አድርገው ፊቴን ይፈልጋሉ።


ጌታ፥ “በፀሐይ ጮራ እንደ ደረቅ ትኩሳት፥ በአጨዳም ወራት እንደ ጠል ደመና ሆኜ በማደሪያዬ በጸጥታ ተቀምጬ እመለከታለሁ” ብሎኛል።


ፍርድን የምትወድ ኃያል ንጉሥ፥ አንተ ቅንነትን አጸናህ፥ በያዕቆብ ፍርድንና ጽድቅን አንተ ፈጽምህ።


ጌታ አምላክ ፀሐይና ጋሻ ነው፥ ሞገስንና ክብርን ይሰጣል፥ ጌታ በቅንነት የሚሄዱትን ከመልካም ነገር አያስቀራቸውም።


እንዲያውም፦ ‘አላየውም፥ ጉዳዩ በእርሱ ፊት ነው፥ እኔም አጠብቀዋለሁ’ ስትልማ የባሰ ነው።


“እርሱ ዐለት፥ ሥራውም ፍጹም ነው፤ መንገዱም ሁሉ የቀና ነው፥ የታመነ አምላክ፥ ተንኮል የሌለበት፥ እርሱ ቀጥተኛና ጻድቅ ነው።


እርሷም፦ “ውሽሞቼ ለእኔ የሰጡኝ ዋጋዬ ይህ ነው” ያለችውን ወይንዋንና በለስዋን አጠፋለሁ፤ ዱርም አደርገዋለሁ፥ የምድረ በዳም አራዊት ይበሉታል።


ከድሮ ዘመን ጀምሮ ዝም ብያለሁ፥ ዝም ብዬም ታግሻለሁ፤ አሁን ምጥ እንደ ያዛት ሴት እጮኻለሁ፤ አጠፋለሁ በአንድነትም እጨርሳለሁ።


ጌታን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ ይሮጣሉ፤ አይታክቱም፤ ይሄዳሉ፤ አይደክሙም።


የእብሪተኛ ሰው ዐይን ይሰበራል፤ የሰዎችም ትዕቢት ይዋረዳል፤ በዚያን ቀን ጌታ ብቻውን ከፍ ከፍ ይላል።


የሰው እብሪት ይዋረዳል፤ የሰውም ኩራት ይወድቃል፤ በዚያን ቀን ጌታ ብቻ ከፍ ከፍ ይላል፤


ለገመድ ፍትህን፥ ለቱንቢም ጽድቅን አደርጋለሁ፤ በረዶውም የሐሰትን መሸሸጊያ ይጠርጋል፥ ውኆችም መሰወሪያውን ያሰጥማሉ።


አቤቱ ጌታ ሆይ፥ ማረን፤ አንተን እንጠባበቃለን፤ በየእለቱ ክንዳችን፥ በመከራም ጊዜ መድኅኒት ሁነን።


ዕውሮችንም በማያውቁት መንገድ አመጣቸዋለሁ፤ በማያውቁትም ጎዳና እመራቸዋለሁ፤ በፊታቸውም ጨለማውን ብርሃን አደርጋለሁ፤ ጠማማውንም አቀናለሁ። ይህን አደርግላቸዋለሁ፥ አልተዋቸውም።


ስለ ስሜ ቁጣዬን አዘገያለሁ፥ እንዳለጠፋህም ስለ ምስጋናዬ እታገሣለሁ።


እኔ ጌታ ፍትህን የምወድ፥ ስርቆትንና በደልን የምጠላ ነኝ፤ ፍዳቸውንም በእውነት እሰጣቸዋለሁ፥ ከእነርሱም ጋር የዘለዓለምን ቃል ኪዳን አደርጋለሁ።


ሰዎች ከጥንት ጀምሮ ማንም አልሰሙም፥ የትኛውም ጆሮ አልተቀበለውም፥ ለሚጠብቁህ ከምትሠራላችው ከአንተ አምላካችን በቀር ሌላ ማንም አላየውም።


ከዐሥር ቀን በኋላ የጌታ ቃል ወደ ኤርምያስ መጣ።


ነገር ግን የይሁዳን ቤት እምራለሁ፤ እነርሱንም በቀስት ወይም በሰይፍ ወይም በጦርነት ወይም በፈረሶች ወይም በፈረሰኞች ሳይሆን በአምላካቸው በጌታ አድናቸዋለሁ።”


መንፈስም የፈጠርሁትም ነፍስ ከፊቴ እንዳይዝል ለዘለዓለም አልጣላም፥ ሁልጊዜም አልቈጣም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች