መዝሙር 148:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እሳትና በረዶ አመዳይና ጉም፥ ቃሉን የሚፈጽም ዐውሎ ነፋስም፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እሳትና በረዶ፣ ዐመዳይና ጭጋግ፣ ትእዛዙንም የሚፈጽም ዐውሎ ነፋስ፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እሳትና በረዶ፥ ዐመዳይና ደመና፥ ትእዛዙን የምትፈጽሙም ብርቱዎች ነፋሳት እግዚአብሔርን አመስግኑ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እሳትና በረዶ፥ አመዳይና ውርጭ፥ ቃሉን የሚያደርግ ዐውሎ ነፋስም፤ |
ሙሴም በግብጽ ምድር ላይ በትሩን ዘረጋ፥ ጌታም የምሥራቅን ነፋስ ያን ቀን ሁሉ ሌሊቱን ሁሉ አመጣ፤ በነጋም ጊዜ የምሥራቁ ነፋስ አንበጣዎቹን አመጣ።
ሙሴም በባሕሩ ላይ እጁን ዘረጋ፤ ጌታም ሌሊቱን ሁሉ ጽኑ የምሥራቅ ነፋስ አምጥቶ ባሕሩን አስወገደው፥ ባሕሩንም ደረቅ ምድር አደረገው፥ ውኆችም ተከፈሉ።
“እነሆ፥ ተራሮችን የሠራ፥ ነፋስንም የፈጠረ፥ የልቡንም ሐሳብ ለሰው የሚነግር፥ ንጋትን ጨለማ የሚያደርግ፥ በምድርም ከፍታዎች ላይ የሚረግጥ፥ ስሙ የሠራዊት አምላክ ጌታ ነው።”
መርከበኞቹም ፈሩ፥ እያንዳንዱም ወደ አምላኩ ጮኸ፤ መርከቢቱ እንዲቀልልላቸውም መርከቢቱ ውስጥ የነበሩትን ዕቃዎች ወደ ባሕር ጣሉ፤ ዮናስ ግን ወደ መርከቡ ታችኛው ክፍል ወርዶ ነበር፥ በከባድ እንቅልፍም ተኝቶ ነበር።
ከእስራኤልም ልጆች ፊት እየሸሹ የቤትሖሮንን ቁልቁለት በመውረድ ላይ ሳሉ፥ ዓዜቃ እስኪደርሱ ድረስ ጌታ ከሰማይ ታላላቅ ድንጋይ አወረደባቸውና ሞቱ፤ የእስራኤል ልጆች በሰይፍ ከገደሉአቸው ይልቅ በበረዶ ድንጋይ የሞቱት በለጡ።
በሚዛንም አንድ ታላንት የሚያህል ታላቅ በረዶ በሰዎች ላይ ከሰማይ ወረደባቸው፤ ሰዎቹም ከበረዶው መቅሰፍት የተነሣ እግዚአብሔርን ተሳደቡ፤ መቅሰፍቱ እጅግ ታላቅ ነበርና።