Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 148:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 እሳትና በረዶ፥ ዐመዳይና ደመና፥ ትእዛዙን የምትፈጽሙም ብርቱዎች ነፋሳት እግዚአብሔርን አመስግኑ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 እሳትና በረዶ፣ ዐመዳይና ጭጋግ፣ ትእዛዙንም የሚፈጽም ዐውሎ ነፋስ፣

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 እሳትና በረዶ አመዳይና ጉም፥ ቃሉን የሚፈጽም ዐውሎ ነፋስም፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 እሳ​ትና በረዶ፥ አመ​ዳ​ይና ውርጭ፥ ቃሉን የሚ​ያ​ደ​ርግ ዐውሎ ነፋ​ስም፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 148:8
24 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግዚአብሔር በሰዶምና በገሞራ ከተሞች ላይ እሳትና ዲን ከራሱ (ከእግዚአብሔር ዘንድ) ከሰማይ አዘነበ።


ደመናዎች በጌታ መሪነት በምድር ዙሪያ ይዞራሉ፤ የሚያግዛቸውንም ትእዛዞች ይፈጽማሉ።


ትእዛዞቹን የምትፈጽሙ የሚናገረውን የምታዳምጡ፤ እናንተ ኀያላንና ብርቱዎች መላእክቱ እግዚአብሔርን አመስግኑ።


በፊቱ ካለው ነጸብራቅ በረዶና የእሳት ብልጭታ ጥቅጥቅ ያለውን ደመና ሰንጥቆ ወጣ።


ስለዚህ ሙሴ በግብጽ ምድር ላይ እጁን ዘረጋ፤ እግዚአብሔርም በዚያን ቀንና ሌሊት የምሥራቅ ነፋስ አስነሣ፤ በነጋም ጊዜ ያ የምሥራቅ ነፋስ አንበጦችን አመጣ።


እግዚአብሔርም የምሥራቁን ነፋስ የሚቋቋምና አንበጦቹንም ጠራርጎ ወደ ቀይ ባሕር የሚነዳ ብርቱ ነፋስ ከምዕራብ በኩል አስነሣ፤ በዚህ ዐይነት በመላው የግብጽ ምድር አንድ አንበጣ እንኳ አልቀረም።


ሙሴ እጁን በባሕሩ ላይ ዘረጋ፤ እግዚአብሔርም በብርቱ የምሥራቅ ነፋስ ባሕሩን ወደ ኋላ መለሰው፤ ነፋሱም ሌሊቱን ሙሉ በመንፈሱ፥ ባሕሩን ወደ ደረቅ ምድር ለወጠው፤ ውሃውም ከሁለት ተከፈለ፤


እግዚአብሔር በሰዎች ሁሉ ላይ በእሳትና በሰይፍ ይፈርዳል፤ እንዲሁም በሞት የሚቀጣቸው ብዙዎች ናቸው።


“በሰማይና በምድር፥ ድንቅ ነገሮችን አሳያለሁ፤ ደምና እሳት፥ የጢስ ዐምድም ይታያል።


ከዚህም የተነሣ በድንገት ከእግዚአብሔር ዘንድ የተላከ እሳት ስለ በላቸው በእግዚአብሔር ፊት ሞቱ፤


ተራራዎችን የሠራ፥ ነፋሶችን የፈጠረ፥ ያሰበውን ነገር ለሰው የሚገልጥ፥ የቀኑን ብርሃን ወደ ጨለማ የሚለውጥ፥ በምድር ከፍታዎች ላይ የሚራመድ፥ ስሙ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ነው።


ጌታ እግዚአብሔር የገለጠልኝ ሌላውም ራእይ ይህ ነው፤ እነሆ፥ ጌታ እግዚአብሔር የእሳት ቅጣት ፍርድ አስተላለፈ፤ እሳቱም ባሕሩን በልቶ ካደረቀው በኋላ ምድርን ማቃጠል ጀመረ።


እግዚአብሔር ግን በባሕሩ ላይ ከባድ ነፋስን አስነሣ፤ በባሕሩም ላይ የተቀሰቀሰው ማዕበል ብርቱ ከመሆኑ የተነሣ መርከቢቱ ልትሰበር ተቃረበች፤


መርከበኞቹም እጅግ ስለ ፈሩ እያንዳንዱ ወደ አምላኩ ጮኸ፤ የመርከቢቱን ክብደት ለመቀነስ አስበው በውስጥዋ የነበረውን ዕቃ እያወጡ ወደ ባሕር ጣሉ፤ ዮናስ ግን በመርከቢቱ ታችኛ ክፍል ወርዶ በመተኛቱ በከባድ እንቅልፍ ላይ ነበር።


ከዚያም በኋላ እግዚአብሔር እሳት ልኮ ዕጣን ያጥኑ የነበሩትን ሁለት መቶ ኀምሳ ሰዎች አቃጠለ።


አሞራውያን በመተላለፊያው ቊልቊለት ከእስራኤላውያን ሠራዊት በሚሸሹበት ጊዜ፥ እግዚአብሔር እስከ ዐዜቃ ድረስ ከሰማይ ታላላቅ የበረዶ ድንጋይ አወረደባቸው፤ ስለዚህም እስራኤላውያን ከገደሉአቸው ይልቅ በበረዶው ድንጋይ የሞቱት እጅግ ብዙዎች ነበሩ።


እያንዳንዱ አርባ አምስት ኪሎ ግራም ያኽል የሚመዝን በረዶ ከሰማይ በሰዎች ላይ ወረደ፤ መቅሠፍቱ እጅግ አሠቃቂ ስለ ነበረ ሰዎች በበረዶው መቅሠፍት ምክንያት እግዚአብሔርን ተሳደቡ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች