ዘፀአት 10:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)19 ጌታም ከምዕራብ ዐውሎ ነፋሱን መለሰ፥ አንበጣዎቹንም ወስዶ በኤርትራ ባሕር ውስጥ ጣላቸው፤ አንድ ስንኳ አንበጣ በግብጽ አገር አልቀረም። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም19 ከዚያም እግዚአብሔር ነፋሱን ወደ ብርቱ የምዕራብ ነፋስ ለወጠው፤ ያም ነፋስ አንበጣዎቹን እየነዳ ወደ ቀይ ባሕር ከተታቸው፤ በግብጽ ምድር በየትኛውም ቦታ አንድም አንበጣ አልቀረም። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም19 እግዚአብሔርም የምሥራቁን ነፋስ የሚቋቋምና አንበጦቹንም ጠራርጎ ወደ ቀይ ባሕር የሚነዳ ብርቱ ነፋስ ከምዕራብ በኩል አስነሣ፤ በዚህ ዐይነት በመላው የግብጽ ምድር አንድ አንበጣ እንኳ አልቀረም። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)19 እግዚአብሔርም ከባሕር ዐውሎ ነፋሱን አስወገደ፤ አንበጣዎችንም ወስዶ በኤርትራ ባሕር ውስጥ ጣላቸው፤ አንድ አንበጣም እንኳን በግብፅ ዳርቻ ሁሉ አልቀረም። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)19 እግዚአብሔርም ከምዕራብ ዐውሎ ነፋሱን አስወገደ፤ አንበጣዎቹንም ወስዶ በኤርትራ ባሕር ውስጥ ጣላቸው፤ አንድ አንበጣም በግብፅ ዳርቻ ሁሉ አልቀረም። ምዕራፉን ተመልከት |