ዘፀአት 10:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)13 ሙሴም በግብጽ ምድር ላይ በትሩን ዘረጋ፥ ጌታም የምሥራቅን ነፋስ ያን ቀን ሁሉ ሌሊቱን ሁሉ አመጣ፤ በነጋም ጊዜ የምሥራቁ ነፋስ አንበጣዎቹን አመጣ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም13 ስለዚህ ሙሴ በግብጽ አገር ላይ በትሩን ዘረጋ፤ እግዚአብሔርም በዚያ ቀንና ሌሊት በሙሉ በምድሪቱ ላይ የምሥራቅ ነፋስ እንዲነፍስ አደረገ፤ በማግስቱም ነፋሱ አንበጣዎችን አመጣ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም13 ስለዚህ ሙሴ በግብጽ ምድር ላይ እጁን ዘረጋ፤ እግዚአብሔርም በዚያን ቀንና ሌሊት የምሥራቅ ነፋስ አስነሣ፤ በነጋም ጊዜ ያ የምሥራቅ ነፋስ አንበጦችን አመጣ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)13 ሙሴም በትሩን ወደ ሰማይ ዘረጋ፤ እግዚአብሔርም የደቡብን ነፋስ ያን ቀን ሁሉ ሌሊቱንም ሁሉ አመጣ፤ ማለዳም በሆነ ጊዜ የደቡብ ነፋስ አንበጣን አመጣ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)13 ሙሴም በግብፅ አገር ላይ በትሩን ዘረጋ፤ እግዚአብሔርም የምሥራቅን ነፋስ ያን ቀን ሁሉና ሌሊቱን ሁሉ አመጣ፤ ማለዳም በሆነ ጊዜ የምሥራቁ ነፋስ አንበጣዎቹን አመጣ። ምዕራፉን ተመልከት |