ምሳሌ 18:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጻድቅ ፍርድ ይጠምም ዘንድ፥ ለኀጥእም ማድላት መልካም አይደለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለክፉ ሰው ማድላት፣ ንጹሑንም ፍትሕ መንሣት ተገቢ አይደለም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለበደለኛው ማዳላትና ንጹሕ ሰው ትክክለኛ ፍትሕ እንዳያገኝ ማድረግ ተገቢ አይደለም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የኃጥኣንን ፊት ማድነቅ መልካም አይደለም። በፍርድ ጊዜም እውነትን ማራቅ መልካም አይደለም፥ |
እጆቻቸው ክፉ ለማድረግ የተለማመዱ ናቸው፤ ልዑሉና ፈራጁ ጉቦን ይፈልጋሉ፥ ትልቁም ሰው እንደ ነፍሱ ምኞት ይናገራል፤ እንዲሁም ክፋትን ይጐነጉናሉ።
ደቀ መዛሙርታቸውን ከሄሮድስ ሰዎች ጋር ላኩበት፤ እነርሱም እንዱህ አሉት “መምህር ሆይ! እውነተኛ እንደሆንህ የእግዚአብሔርንም መንገድ በእውነት እንደምታስተምር እናውቃለን፤ ለማንምም አታደላም፤ የሰውን ፊት አታይምና፤