Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ምሳሌ 24:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 እነዚህ ደግሞ የጠቢባን ቃሎች ናቸው። በፍርድ ላይ ማዳለት መልካም አይደለም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 እነዚህም ደግሞ የጠቢባን ምሳሌዎች ናቸው፦ በዳኝነት አድልዎ ማድረግ ተገቢ አይደለም፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 የጥበበኞች ተጨማሪ አባባሎች፦ በዳኝነት ማዳላት ስሕተት ነው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 የነገሩትን የሚጠብቅ ልጅ ከጥፋት የራቀ ነው፥ የሚቀበልም እርሱን ይቀበለዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ምሳሌ 24:23
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ማዳላት መልካም አይደለም፥ አንዳንድ ሰው ግን ለቁራሽ ሲል ጥፋት ይፈጽማል።


የጻድቅ ፍርድ ይጠምም ዘንድ፥ ለኀጥእም ማድላት መልካም አይደለም።


ጠቢብ ማነው? ይህንን ይፈጽም፥ እርሱ የጌታንም ጽኑ ፍቅር ይገነዘባል።


“ፍርድን ፈጽሞ አታጓድሉ፤ ለድሀ አታድላ፥ ባለ ጠጋውንም አታክብር፤ ነገር ግን ለባልንጀራህ በጽድቅ ፍረድ።


ለሰው ፊትም ሳያደላ በእያንዳንዱ ላይ እንደ ሥራው የሚፈርደውን አባት ብላችሁ የምትጠሩት ከሆነ፥ በእንግድነታችሁ ዘመን በፍርሃት ኑሩ።


ከላይ የሆነችው ጥበብ ግን በመጀመሪያ ንጽሕት ናት፤ ቀጥሎም ሰላም ወዳድ፥ ደግ፥ እሺ ባይ፥ ምሕረትና መልካም ፍሬ የሞላባት፥ ጥርጥርና ግብዝነት የሌለባት ናት።


ቅን ፍርድ ፍረዱ እንጂ በመልክ አትፍረዱ።”


ኤፍሬም ሆይ! ከእንግዲህ ወዲህ ከጣዖታት ጋር እኔ ምን አደርጋለሁ? እኔ እመልስለታለሁ፥ ወደ እርሱም እመለከታለሁ፤ እኔ እንደ ለመለመ ጥድ ነኝ፤ ፍሬህ በእኔ ዘንድ ይገኛል።


ምሳሌንና ምሥጢርን የጠቢባንን ቃልና ዕንቆቅልሸ ለማስተዋል።


እንግዲህ አሁን ጌታን መፍራት በእናንተ ላይ ይሁን፤ በአምላካችንም በጌታ ዘንድ በደልና ለሰው ፊት ማድላት መማለጃም መውሰድ የለምና ሁሉንም ነገር ተጠንቅቃችሁ አድርጉ።”


ፍርድ አታዛባ፤ አድልዎ አታድርግ፤ ጉቦ የጠቢባንን ዐይን ያሳውራል፤ የጻድቃንንም ቃል ያጣምማልና ጉቦም አትቀበል።


በፍርድም አድልዎ አታድርጉ፥ ታላቁን እንደምትሰሙ፥ ታናሹንም እንዲሁ ስሙ፥ ፍርድ ለእግዚአብሔር ነውና ከሰው ፊት አትፍሩ፥ አንድ ነገር ቢከብዳችሁ እርሱን ወደ እኔ አምጡት፥ እኔም እሰማዋለሁ፤’


ጆሮህን አዘንብለህ የጠቢባንን ቃላት ስማ፥ ልብህንም ወደ እውቀቴ አድርግ፥


ለእርሱ እያዳላችሁ ነውን? ስለ እግዚአብሔርስ ትከራከራላችሁን?


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች