Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ምሳሌ 18:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 የሰነፍ ከንፈር በጥል ውስጥ ትገባለች፥ አፉም በትርን ትጠራለች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 የሞኝ ከንፈር ጠብ ያመጣበታል፤ አፉም በትር ይጋብዛል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 የሞኝ ንግግር ጠብን ያነሣሣል፤ ልፍለፋውም በትርን ይጋብዛል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 አላዋቂን ከንፈሮቹ ወደ ክፉ ያደርሱታል፥ የችኩል አፍም ሞትን ይጠራል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ምሳሌ 18:6
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የሰነፍ ቁጣ ቶሎ ይታወቃል፥ ብልህ ሰው ግን ነውርን ይሰውራል።


በትዕቢት ጠብ ብቻ ይሆናል፥ ጥበብ ግን ምክርን በሚቀበሉ ዘንድ ናት።


ጠቢብ ሰው ይፈራል ከክፉም ይሸሻል፥ ሰነፍ ግን ራሱን ታምኖ ይኰራል።


በሰነፍ አፍ የትዕቢት በትር አለ፥ የጠቢባን ከንፈር ግን ትጠብቃቸዋለች።


የጠብ መጀመሪያ እንደ ውኃ አፈሳሰስ ነው፥ ስለዚህ ጠብ ሳይበረታ አንተ ክርክርን ተው።


ንዴተኛ ሰው መቀጮ ይከፍላል፥ ብታድነውም ደግሞ ትጨምራለህ።


ለሚያፌዙ ሰዎች ፍርድ ተዘጋጅታለች፥ ለሰነፎችም ጀርባ በትር።


ከክርክር ይርቅ ዘንድ ለሰው ክብሩ ነው፥ ሰነፍ ሁሉ ግን እንዲህ ባለ ነገር ይጣመራል።


ፌዘኛን ብታስወጣ ክርክር ይቆማል፥ ጠብና ስድብም ያልቃል።


ከጠበኛ ሴት ጋር በአንድ ቤት ውስጥ ከመቀመጥ በሰገነት ማዕዘን ላይ መቀመጥ ይሻላል።


ድንጋይ ከባድ ነው አሸዋም እንዲሁ፥ ከሁለቱ ግን የሞኝ ቁጣ ይከብዳል።


ጠቢብ ከሞኝ ጋር ቢጣላ፥ ሞኙ ወይም ይቈጣል ወይም ይስቃል፥ ዕረፍትም አይኖርም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች