ነህምያ 8:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዕዝራም ታላቁን አምላክ ጌታን ባረከ፤ ሕዝቡም ሁሉ እጆቻቸውን በመዘርጋት፦ አሜን፥ አሜን ብለው መለሱ። ራሳቸውን አዘነበሉ፥ በግምባራቸውም ተደፍተው ለጌታ ሰገዱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዕዝራም ታላቁን አምላክ እግዚአብሔርን አመሰገነ፤ ሕዝቡም ሁሉ እጆቻቸውን በማንሣት፣ “አሜን! አሜን!” ብለው መለሱ፤ ከዚህ በኋላ በግምባራቸው ወደ መሬት ተደፍተው ለእግዚአብሔር ሰገዱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዕዝራም ታላቁን አምላክ እግዚአብሔርን አመሰገነ። ሁሉም እጆቻቸውን ወደ ላይ በማንሣት “አሜን! አሜን!” ሲሉ መለሱ፤ ወደ ምድርም ለጥ ብለው ለእግዚአብሔር ሰገዱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዕዝራም ታላቁን አምላክ እግዚአብሔርን አመሰገነ፤ ሕዝቡም ሁሉ እጃቸውን እየዘረጉ፥ “አሜን፥ አሜን” ብለው መለሱ። ራሳቸውንም አዘነበሉ፤ በግንባራቸውም ወደ ምድር ተደፍተው ለእግዚአብሔር ሰገዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዕዝራም ታላቁን አምላክ እግዚአብሔርን ባረከ ሕዝቡም ሁሉ እጃቸውን እየዘረጉ፦ አሜን፥ አሜን ብለው መለሱ። ራሳቸውንም አዘነበሉ፥ በግምባራቸውም ተደፍተው ለእግዚአብሔር ሰገዱ። |
ዳዊትም በጉባኤው ሁሉ ፊት ጌታን ባረከ፤ ዳዊትም እንዲህ አለ፦ “አቤቱ፥ የአባታችን የእስራኤል አምላክ ሆይ! ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ተባረክ።
ዳዊትም ጉባኤውን ሁሉ፦ “አምላካችሁን ጌታን ባርኩ” አላቸው። ጉባኤውም ሁሉ የአባቶቻቸውን አምላክ ጌታን ባረኩ፥ ራሳቸውንም አዘንብለው ለጌታና ለንጉሡ ሰገዱ።
ንጉሡም ሕዝቅያስና ሹማምንቱ ሌዋውያንን በዳዊትና በባለ ራእዩ በአሳፍ ቃል ጌታን እንዲያመሰግኑ አዘዙ። በደስታም እያመሰገኑ፥ አጐነበሱም ሰገዱም።
እርሱም እንዲህ አለ፦ “ለአባቴ ለዳዊት እንዲህ ብሎ በአፉ የተናገረው በእጁም የፈፀመው የእስራኤል አምላክ ጌታ ይባረክ፤ እርሱም እንዲህ አለው፦
ደግሞም ልብሴን አራገፍሁና፦ “ይህን ቃል የማይፈጽመውን ሰው እግዚአብሔር ከቤቱና ከንብረቱ እንደዚሁ ያራግፈው፤ እንዲሁም የተራገፈና ባዶ ይሁን” አልሁ። ጉባኤውም ሁሉ፦ “አሜን” አሉና ጌታን አመሰገኑ፤ ሕዝቡ ቃል ኪዳኑ አደረጉ።
ደግሞ ኢያሱ፥ ባኒ፥ ሼሬብያ፥ ያሚን፥ ዓቁብ፥ ሻብታይ፥ ሆዲያ፥ ማዓሤያ፥ ቅሊጣ፥ አዛርያ፥ ዮዛባድ፥ ሐናን፥ ፐላያና ሌዋውያኑ ሕጉን ለሕዝቡ ያስረዱ ነበር፤ ሕዝቡም በቆሙበት ነበሩ።
እናንተም፦ ‘ለጌታ የፋሲካ መሥዋዕት ነው፥ በግብጽ በእስራኤል ልጆች ቤቶች ላይ አልፎ ግብፃዊያንን በመታ ጊዜ፥ ቤቶቻችንን ያዳነበት ነው’ ትሉአቸዋላችሁ።” ሕዝቡም ተጎነበሱ ሰገዱም።
ነቢዩም ኤርምያስ እንዲህ አለ፦ “አሜን፥ ጌታ እንዲህ ያድርግ፤ የጌታን ቤት ዕቃዎችና ምርኮውን ሁሉ ከባቢሎን ወደዚህ ስፍራ በመመለስ ጌታ የተናገርኸውን የትንቢት ቃላት ይፈጽም።
እሳትም ከጌታ ዘንድ ወጣ፥ በመሠዊያውም ላይ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ስቡንም በላ፤ ሕዝቡም ሁሉ አይተው እልል አሉ፥ በግምባራቸውም ተደፍተው ሰገዱ።
ወደ ፊት ጥቂት እልፍ ብሎ በፊቱ ተደፋና እንዲህ ሲል ጸለየ “አባቴ! የሚቻል ከሆነ፥ ይህች ጽዋ ከእኔ ትለፍ፤ ነገር ግን እንደ አንተ ፈቃድ እንጂ እንደ እኔ አይሁን።”
እንዲህማ ካልሆነ፥ በመንፈስ በምትባርክበት ጊዜ፥ አንተ የምትለውን የማያውቅ እንግዳ ሰው ካልተረዳ፥ እንዴት አድርጎ ለምስጋናህ፥ “አሜን” ሊል ይችላል?
ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ ሕያው የሆነውን ተስፋ የሰጠን፥ ከምሕረቱ ብዛት በአዲስ ልደት ልጆቹ ያደረገን፥ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ እና አባት ይመስገን፤
መላእክቱም ሁሉ በዙፋኑና በሽማግሌዎቹ በአራቱም ሕያዋን ፍጡራን ዙሪያ ቆመው ነበር፤ በዙፋኑም ፊት በግምባራቸው ተደፉ፤ ለእግዚአብሔርም እየሰገዱ