ዘሌዋውያን 9:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)24 እሳትም ከጌታ ዘንድ ወጣ፥ በመሠዊያውም ላይ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ስቡንም በላ፤ ሕዝቡም ሁሉ አይተው እልል አሉ፥ በግምባራቸውም ተደፍተው ሰገዱ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም24 እሳት ከእግዚአብሔር ዘንድ ወጥቶ፣ በመሠዊያው ላይ የነበረውን በላ፤ ሕዝቡም ሁሉ ይህን ባዩ ጊዜ እልል አሉ፤ በግንባራቸውም ተደፉ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም24 እሳትም በድንገት ከእግዚአብሔር ዘንድ ተልኮ፥ በመሠዊያው ላይ የነበረውን መሥዋዕትና ስብ ሁሉ በላ፤ ሕዝቡ ሁሉ ይህን ባዩ ጊዜ እልል አሉ፤ በምድር ላይም በግንባራቸው ተደፍተው ሰገዱ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)24 እሳትም ከእግዚአብሔር ዘንድ ወጣ፤ በመሠዊያውም ላይ የሚቃጠለውን መሥዋዕት፥ ስቡንም በላ፤ ሕዝቡም ሁሉ አይተው ተደነቁ፤ በግምባራቸውም ወደቁ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)24 እሳትም ከእግዚአብሔር ዘንድ ወጣ፥ በመሠዊያውም ላይ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ስቡንም በላ፤ ሕዝቡም ሁሉ አይተው እልል አሉ፥ በግምባራቸውም ወደቁ። ምዕራፉን ተመልከት |