Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፀአት 12:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 እናንተም፦ ‘ለጌታ የፋሲካ መሥዋዕት ነው፥ በግብጽ በእስራኤል ልጆች ቤቶች ላይ አልፎ ግብፃዊያንን በመታ ጊዜ፥ ቤቶቻችንን ያዳነበት ነው’ ትሉአቸዋላችሁ።” ሕዝቡም ተጎነበሱ ሰገዱም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 ‘ግብጻውያንን በቀሠፈ ጊዜ፣ በግብጽ ምድር የእስራኤላውያንን ቤት ዐልፎ በመሄድ ቤታችንን ላተረፈ፣ ለእግዚአብሔር የፋሲካ መሥዋዕት ነው’ ብላችሁ ንገሯቸው።” ከዚያም ሕዝቡ አጐነበሱ፤ ሰገዱም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 እናንተም እንዲህ ብላችሁ ትመልሱላቸዋላችሁ፤ ‘ይህ እግዚአብሔርን ለማክበር የሚደረግ የፋሲካ መሥዋዕት ነው፤ እግዚአብሔር በግብጽ ምድር የእስራኤላውያንን መኖሪያ ቤቶች አልፎ በመሄድ ግብጻውያንን ሲገድል እኛን አድኖናል።’ ” እስራኤላውያንም ይህን በሰሙ ጊዜ ተንበርክከው ሰገዱ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 ‘ይህ በግ​ብፅ ሀገር የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ቤቶች ሰውሮ ግብ​ፃ​ው​ያ​ንን በመታ ጊዜ፥ ቤቶ​ቻ​ች​ንን የአ​ዳነ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የፋ​ሲ​ካው መሥ​ዋ​ዕት ነው’ ትሉ​አ​ቸ​ዋ​ላ​ችሁ።” ሕዝ​ቡም ተጐ​ነ​በሱ፤ ሰገ​ዱም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 ባሉአችሁ ጊዜ፥ እናንተ፦ ‘በግብፅ አገር በእስራኤል ልጆች ቤቶች ላይ አልፎ ግብፃዊያንን በመታ ጊዜ፥ ቤቶቻችንን ያዳነ የእግዚአብሔር የማለፉ መሥዋዕት ይህች ናት’ ትሉአቸዋላችሁ።” ሕዝቡም ተጎነበሰ ሰገደም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፀአት 12:27
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሕዝቡም አመኑ፤ ጌታ የእስራኤልን ልጆች እንደተመለከተ ጭንቀታቸውንም እንዳየ በሰሙ ጊዜ፥ አጎነበሱ ሰገዱም።


እንግዲህ ወገቦቻችሁን ታጥቃችሁ፥ ጫማችሁን በእግራችሁ፥ በትራችሁንም በእጃችሁ አድርጋችሁ ብሉት፥ ፈጥናችሁም ብሉት፤ ለጌታ ፋሲካ ነው።


እንግዲህ እርሾ እንደሌለበት እንደ አዲስ ሊጥ እንድትሆኑ፥ አሮጌውን እርሾ አስወግዱ። ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዶአልና፤


ጌታ ግብጽን ሊመታ ያልፋል፤ ደሙንም በጉበኖቹና በሁለቱ መቃኖች ላይ ያያል፥ ጌታም በበሩ ያልፋል፥ አጥፊውም ሊመታችሁ ወደ ቤታችሁ እንዲገባ አይፈቅድም።


ዕዝራም ታላቁን አምላክ ጌታን ባረከ፤ ሕዝቡም ሁሉ እጆቻቸውን በመዘርጋት፦ አሜን፥ አሜን ብለው መለሱ። ራሳቸውን አዘነበሉ፥ በግምባራቸውም ተደፍተው ለጌታ ሰገዱ።


ንጉሡም ሕዝቅያስና ሹማምንቱ ሌዋውያንን በዳዊትና በባለ ራእዩ በአሳፍ ቃል ጌታን እንዲያመሰግኑ አዘዙ። በደስታም እያመሰገኑ፥ አጐነበሱም ሰገዱም።


ኢዮሣፍጥም በግንባሩ ወደ ምድር ሰገደ ይሁዳም ሁሉ በኢየሩሳሌምም የሚኖሩ በጌታ ፊት በምድር በግንባራቸው ተደፍተው ለጌታ ሰገዱ።


ዳዊትም ጉባኤውን ሁሉ፦ “አምላካችሁን ጌታን ባርኩ” አላቸው። ጉባኤውም ሁሉ የአባቶቻቸውን አምላክ ጌታን ባረኩ፥ ራሳቸውንም አዘንብለው ለጌታና ለንጉሡ ሰገዱ።


“አምላክህ ጌታ በሚሰጥህ በማናቸውም ከተማ ፋሲካን መሠዋት አይገባህም፤


ጌታ ለስሙ ማደሪያ እንዲሆን በሚመርጠው ስፍራ ከበግና ከፍየል ወይም ከመንጋህ አንዱን እንስሳ ለጌታ ለእግዚአብሔር ፋሲካ አድርገህ ሠዋ።


“የመሥዋዕቴን ደም እርሾ ካለው ቂጣ ጋር አትሠዋ፤ የፋሲካው በዓል መሥዋዕት እስከ ማለዳ አይደር።


ሙሴም ፈጥኖ ወደ መሬት ተደፍቶ ሰገደ፦


ይህም በልጅህና በልጅ ልጅህ ጆሮ እንድትነግርና ግብፃውያንን እንዴት እንዳሞኘኋቸው፥ በመካከላቸው ያስቀመጥኩት ምልክቶቼም ጌታ እንደሆንኩ እንድታውቁ ነው።”


የእስራኤልም ልጆች ሄዱ፥ እንዲሁም አደረጉ፤ ጌታ ሙሴንና አሮንን እንዳዘዘ እንዲሁ አደረጉ።


እንዲህም ይሆናል በሚመጣው ጊዜ ልጅህ፦ ይህ ምንድነው? ብሎ በጠየቀህ ጊዜ እንዲህ ትለዋለህ፦ ጌታ በብርቱ እጅ ከባርነት ቤት ከግብጽ አወጣን፤


ለመዘምራን አለቃ፥ የቆሬ ልጆች ትምህርት።


በዚያም ቀን፦ “ከግብጽ በወጣሁ ጊዜ ጌታ ስላደረገልኝ ነው” ስትል ለልጅህ ትነግረዋለህ።


ለልጆቻቸው ያስታውቅ ዘንድ ለአባቶቻችን ያዘዘውን ምስክር በያዕቆብ አቆመ፥ በእስራኤልም ሕግን ሠራ፥


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች