ማቴዎስ 7:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ስለዚህ ይህን ቃሌን ሰምቶ የሚያደርገው ሁሉ ቤቱን በዓለት ላይ የሠራ ጠቢብ ሰውን ይመስላል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እንግዲህ ይህን ቃሌን ሰምቶ በተግባር የሚያውል፣ ቤቱን በዐለት ላይ የሠራን ብልኅ ሰው ይመስላል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ይህን ቃሌን ሰምቶ በሥራ ላይ የሚያውለው ሁሉ፥ ቤቱን በድንጋይ መሠረት ላይ የሠራ ብልኅ ሰውን ይመስላል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ስለዚህ ይህን ቃሌን ሰምቶ የሚያደርገው ሁሉ ቤቱን በዐለት ላይ የሠራ ልባም ሰውን ይመስላል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ ይህን ቃሌን ሰምቶ የሚያደርገው ሁሉ ቤቱን በዓለት ላይ የሠራ ልባም ሰውን ይመስላል። |