Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ምሳሌ 12:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ክፉ ሰዎች ይወድቃሉ፥ ፈጽሞም አይገኙም፥ የጻድቃን ቤት ግን ጸንቶ ይኖራል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ክፉ ሰዎች ይገለበጣሉ፤ ድራሻቸውም ይጠፋል፤ የጻድቃን ቤት ግን ጸንቶ ይኖራል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ዐመፀኞች ወድቀው ደብዛቸው ይጠፋል የደጋግ ሰዎች ትውልድ ግን ጸንቶ ይኖራል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ኀጢአተኛ በተገለበጠበት ይጠፋል፥ የጻድቃን ቤቶች ግን ጸንተው ይኖራሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ምሳሌ 12:7
20 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ክፉ ሰው በእርግጠኛነት ሳይቀጣ አይቀርም፥ የጻድቃን ዘር ግን ይድናል።


ዐውሎ ነፋስ ሲያልፍ ክፉ ሰው አይገኝም፥ ጻድቅ ግን የዘለዓለም መሠረት ነው።


የክፉዎች ዐይን ግን ትጨልማለች፥ የሚሸሹበትንም ያጣሉ፥ ተስፋቸውም ነፍስን አሳልፎ መስጠት ነው።”


ስለዚህ ስምህ ለዘለዓለም ታላቅ ይሆናል፤ ‘የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የእስራኤል አምላክ ነው!’ ይባላል። የአገልጋይህ የዳዊትም ቤት በፊትህ የጸና ይሆናል።


ቤትህና መንግሥትህ በፊቴ ለዘለዓለም ጸንቶ ይኖራል፤ ዙፋንህም ለዘለዓለም የጸና ይሆናል።’ ”


ጌታ የትዕቢተኞችን ቤት ይነቅላል፥ የባልቴትን ዳርቻ ግን ያጸናል።


የኀጥኣን ቤት ይፈርሳል፥ የቅኖች ማደሪያ ግን ያብባል።


ብልሃተኛ ሴት ቤትዋን ትሠራለች፥ ሰነፍ ሴት ግን በእጅዋ ታፈርሰዋለች።


ጥቂት ጊዜ ቆይቶ፥ ክፉ አድራጊ አይኖርም፥ ትፈልገዋለህ ቦታውንም አታገኝም።


ሥራቸውን ያውቃል፥ በሌሊት ይገለባብጣቸዋል፤ እነርሱም ይደቃሉ።


ሰው በጥበቡ ይመሰገናል፥ ልቡ ጠማማ የሆነ ሰው ግን ይናቃል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች