ማቴዎስ 6:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ሰዎች እንዲያዩላችሁ ብላችሁ መልካምም ሥራችሁን በፊታቸው እንዳታደርጉ ተጠንቀቁ፤ አለበለዚያ በሰማያት ካለው አባታችሁ ዘንድ ሽልማት አታገኙም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ሰዎች እንዲያዩላችሁ፣ መልካም ሥራችሁን በፊታቸው ከማድረግ ተጠንቀቁ፤ እንዲህ ካደረጋችሁ ከሰማዩ አባታችሁ ዋጋ አታገኙም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “ሰዎች ይዩልን ብላችሁ መልካም ሥራችሁን በሰዎች ፊት ከማድረግ ተጠንቀቁ፤ አለበለዚያ ግን፥ በሰማይ አባታችሁ ዘንድ ምንም ዋጋ አታገኙም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ለሰዎች ትታዩ ዘንድ ምጽዋታችሁን በፊታቸው እንዳታደርጉ ተጠንቀቁ፤ ያለዚያ በሰማያት ባለው አባታችሁ ዘንድ ዋጋ የላችሁም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለሰዎች ትታዩ ዘንድ ምጽዋታችሁን በፊታቸው እንዳታደርጉ ተጠንቀቁ፤ ያለዚያ በሰማያት ባለው አባታችሁ ዘንድ ዋጋ የላችሁም። |
ኢዩ ግን ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ሕግ በፍጹም ልቡ ታዛዥ ሆኖ አልተገኘም፤ ይህን በማድረግ ፈንታ እስራኤልን ወደ ኃጢአት የመራቸውን የኢዮርብዓምን ክፉ አርአያነት ተከተለ።
ሕዝብ እንደሚመጣ ወደ አንተ ይመጣሉ፥ እንደ ሕዝቤም በፊትህ ይቀመጣሉ፥ ቃልህንም ይሰማሉ ነገር ግን አያደርጉትም፤ በአፋቸው ብዙ ፍቅር ይገልጣሉ፥ ልባቸው ግን ያልተገባ ጥቅማቸውን ይከተላልና።
ለምድሩ ሕዝብና ለካህናት ለሁሉም እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ በዚህ በሰባው ዓመት በአምስተኛውና በሰባተኛው ወር ስትጾሙና ስታለቅሱ፥ በውኑ ለእኔ ነው የጾማችሁልኝ?
“እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን! መንግሥተ ሰማያትን በሰዎች ፊት ስለምትዘጉ ወዮላችሁ፤ እናንተ ራሳችሁ አትገቡም፤ የሚገቡትንም እንዳይገቡ ትከለክላላችሁ።
ንጉሡም እንዲህ ሲል ይመልስላቸዋል ‘እውነት እላችኋለሁ፤ ከሁሉ ለሚያንሱት ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ያደረጋችሁት ለእኔ እንዳደረጋችሁት ነው።’
በዚያን ጊዜ፥ በሺዎች የሚቈጠሩ ሰዎች ተሰብስበው ከብዛታቸው የተነሣ እየተረጋገጡ ሳለ፥ በቅድሚያ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ ይል ጀመር፦ ከፈሪሳውያን እርሾ ተጠንቀቁ፤ እርሱም ግብዝነት ነው።
እንዲህም አላቸው “ራሳችሁን በሰው ፊት የምታጸድቁ እናንተ ናችሁ፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ልባችሁን ያውቃል፤ በሰው ዘንድ የከበረ በእግዚአብሔር ፊት ርኩሰት ነውና።
ጴጥሮስም አይቶ ለሕዝቡ እንዲህ ሲል መለሰ “የእስራኤል ሰዎች ሆይ! በዚህ ስለምን ትደነቃላችሁ? ወይስ በገዛ ኀይላችን ወይስ እግዚአብሔርን በመፍራታችን ይህ ይመላለስ ዘንድ እንዳደረግነው ስለምን ትኩር ብላችሁ ታዩናላችሁ?
እግዚአብሔር፥ ቅዱሳንን ስላገለገላችሁ እስከ አሁንም ስለምታገለግሉአቸው፥ ያደረጋችሁትን ሥራ ለስሙም ያሳያችሁትን ፍቅር ይረሳ ዘንድ ዐመፀኛ አይደለምና።