ከእነርሱም አንዱ “ንጉሥ ሆይ፥ ከእኛ መካከል ይህን የሚያደርግ ማንም የለም፤ በመኝታ ክፍልህ እንኳ ሆነህ የምትናገረውን ሁሉ ሳይቀር ለእስራኤል ንጉሥ ምሥጢሩን የሚገልጥለት ኤልሳዕ የተባለው ነቢይ ነው” ሲል መለሰለት።
መክብብ 10:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሰማይ ወፍ ቃሉን ይወስደዋልና፥ ባለ ክንፎችም ነገሩን ይናገራሉና በልብህ አሳብ እንኳ ቢሆን ንጉሥን አትስደብ፥ በመኝታ ቤትህም ባለጠጋን አትስደብ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሐሳብህም እንኳ ንጉሥን አትንቀፍ፤ በመኝታ ክፍልህም ባለጠጋን አትርገም፤ የሰማይ ወፍ ቃልህን ልትወስድ፣ የምትበረዋም ወፍ የምትለውን ልታደርስ ትችላለችና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሚሰማብኝ የለም ብለህ በስውር እንኳ ቢሆን ንጉሥን አትማ፤ በተኛህበት አልጋህ ላይ ሆነህም ባለጸጋን አትስደብ፤ ምሥጢርህን የሰሙ ነገር ጠላፊዎች ክንፍ እንዳለው ወፍ በረው ሊነግሩብህ ይችላሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሰማይ ዎፍ ቃልህን ያወጣዋልና፥ ክንፍ ያለውም ነገርህን ያወራዋልና በልብህ ዐሳብ እንኳን ቢሆን ንጉሥን አትሳደብ፥ በመኝታ ቤትህም ባለጠጋን አትሳደብ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሰማይ ወፍ ቃሉን ይወስደዋልና፥ ባለ ክንፎችም ነገሩን ይናገራሉና በልብህ አሳብ እንኳ ቢሆን ንጉሥን አትስደብ፥ በመኝታ ቤትህም ባለጠጋን አትስደብ። |
ከእነርሱም አንዱ “ንጉሥ ሆይ፥ ከእኛ መካከል ይህን የሚያደርግ ማንም የለም፤ በመኝታ ክፍልህ እንኳ ሆነህ የምትናገረውን ሁሉ ሳይቀር ለእስራኤል ንጉሥ ምሥጢሩን የሚገልጥለት ኤልሳዕ የተባለው ነቢይ ነው” ሲል መለሰለት።
ማርታ ግን አገልግሎት ስለ በዛባት ባከነች፤ ቀርባም፦ “ጌታ ሆይ! እኅቴ ብቻዬን እንዳገለግል ስትተወኝ አይገድህምን? እንግዲያውስ እንድታግዘኝ ንገራት፤” አለችው።