Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




መክብብ 11:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 እንጀራህን በውኃ ላይ ጣለው፥ ከብዙ ቀን በኋላ ታገኛዋለህና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 እንጀራህን በውሃ ላይ ጣል፤ ከብዙ ቀን በኋላ መልሰህ ታገኘዋለህና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 እንጀራህን በውሃ ላይ ጣል፤ ከብዙ ቀንም በኋላ መልሰህ ታገኘዋለህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 እን​ጀ​ራ​ህን በውኃ ፊት ላይ ጣለው፥ ከብዙ ቀን በኋላ ታገ​ኝ​ኘ​ዋ​ለ​ህና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 እንጀራህን በውኃ ፊት ላይ ጣለው፥ ከብዙ ቀን በኋላ ታገኛዋለህና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መክብብ 11:1
21 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ማር፥ እርጎ፥ በጎችና የላም አይብ እንዲበሉ ለዳዊትና ለሕዝቡ አመጡላቸው፤ ይህን ያደረጉትም፥ “ሕዝቡ በምድረ በዳ ተርቧል፤ ደክሞአል፤ ተጠምቶአል” ብለው ነው።


ክፉ ሰው የሐሰት ደመወዝ ያገኛል፥ ጽድቅን የሚዘራ ግን የታመነ ዋጋ አለው።


ለድሀ ቸርነትን የሚያደርግ ለጌታ ያበድራል፥ በጎነቱንም መልሶ ይከፍለዋል።


ርኅሩህ የተባረከ ይሆናል፥ ከእንጀራው ለድሀ ሰጥቶአልና።


ወይም ይህ ወይም ያ ማናቸው እንዲበቅል ወይም ሁለቱ መልካም እንዲሆኑ አታውቅምና በማለዳ ዘርህን ዝራ፥ በማታም እጅህን አትተው።


ለመፈለግ ጊዜ አለው፥ ለማጥፋትም ጊዜ አለው፥ ለመጠበቅ ጊዜ አለው፥ ለመጣልም ጊዜ አለው፥


እናንተ የበሬና የአህያ እግር እየነዳችሁ በውሃ ዳርቻ የምትዘዋወሩ ምን ያህል ትደሰቱ!


ከበርቴ ሰው ግን ለመከበር ያስባል፤ ለመከበርም ጸንቶ ይኖራል።


የተትረፈረፈም ፍሬ አብዝተው እንዲሰጡዋችሁ የአምስተኛውን ዓመት ፍሬ ብሉ፤ እኔ ጌታ አምላካችሁ ነኝ።


ቤቱ የተገባው ከሆነ ሰላማችሁ በእርሱ ላይ ይሁን፤ ያልተገባው ከሆነ ግን ሰላማችሁ ወደ እናንተ ይመለስ።


ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ውሃ በደቀ መዝሙር ስም ብቻ የሚያጠጣ፥ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋውን አያጣም።”


እንዲሁም ሁለት የተቀበለው ሌላ ሁለት አተረፈ።


ንጉሡም እንዲህ ሲል ይመልስላቸዋል ‘እውነት እላችኋለሁ፤ ከሁሉ ለሚያንሱት ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ያደረጋችሁት ለእኔ እንዳደረጋችሁት ነው።’


የሚመልሱት አጸፋ የላቸውምና ብፁዕ ትሆናለህ፤ በጻድቃን ትንሣኤ ይመለስልሃልና።”


ይህን አስታውሱ፤ በጥቂት የዘራ ጥቂት ያጭዳል፤ ብዙ የዘራም ብዙ ያጭዳል።


እግዚአብሔር፥ ቅዱሳንን ስላገለገላችሁ እስከ አሁንም ስለምታገለግሉአቸው፥ ያደረጋችሁትን ሥራ ለስሙም ያሳያችሁትን ፍቅር ይረሳ ዘንድ ዐመፀኛ አይደለምና።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች