በታላቅ ኃይልና በሥልጣን ከግብጽ ምድር ላወጣኋችሁ ለእኔ ለእግዚአብሔር ታዛዦች ሁኑ፤ መስገድና መሥዋዕት ማቅረብ የሚገባችሁ ለእኔ ብቻ ነው፤
ዘዳግም 6:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያን ጊዜ ከግብጽ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣህን ጌታ እንዳትረሳ ተጠንቀቅ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከባርነት ምድር ከግብጽ ያወጣህን እግዚአብሔርን እንዳትረሳ ተጠንቀቅ! አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባሪያ ሆነህ ትኖርባት ከነበረችው ከግብጽ ምድር ያወጣህን እግዚአብሔርን እንዳትረሳ ጥንቃቄ አድርግ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣህን እግዚአብሔርን እንዳትረሳ ተጠንቀቅ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያን ጊዜ ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣህን እግዚአብሔርን እንዳትረሳ ተጠንቀቅ። |
በታላቅ ኃይልና በሥልጣን ከግብጽ ምድር ላወጣኋችሁ ለእኔ ለእግዚአብሔር ታዛዦች ሁኑ፤ መስገድና መሥዋዕት ማቅረብ የሚገባችሁ ለእኔ ብቻ ነው፤
እንዲህም ይሆናል በሚመጣው ጊዜ ልጅህ፦ ይህ ምንድነው? ብሎ በጠየቀህ ጊዜ እንዲህ ትለዋለህ፦ ጌታ በብርቱ እጅ ከባርነት ቤት ከግብጽ አወጣን፤
ሙሴም ሕዝቡን አለ፦ ከባርነት ቤት ከግብጽ የወጣችሁበትን ይህንን ቀን አስቡ፥ ጌታ ከዚህ ቦታ በብርቱ እጅ አውጥቶአችኋልና ስለዚህ የቦካ እንጀራ አትብሉ።
ስለዚህም ለእስራኤል ልጆች እንዲህ በላቸው፦ ‘እኔ ጌታ ነኝ፥ ከግብፃውያን ጭቆና አወጣችኋለሁ፥ ከተገዥነታችሁም አላቅቃችኋለሁ፤ በተዘረጋች ክንድ በታላቅ የፍርድ ሥራም አድናችኋለሁ፤
ሰማያትን የዘረጋውን ምድርንም የመሠረተውን ፈጣሪህን ጌታን ረስተሃል፤ ያጠፋ ዘንድ ባዘጋጀ ጊዜ ከአስጨናቂው ቁጣ የተነሣ ሁልጊዜ ቀኑን ሁሉ ፈርተሃል፤ የአስጨናቂው ቁጣ የት አለ? ምርኮኛው ፈጥኖ ይፈታል፤
“የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ አባቶቻችሁን ከባርነት ቤት ከግብጽ አገር ባወጣኋቸው ቀን ከእነርሱ ጋር እንዲህ ብዬ ቃል ኪዳን አደረግሁ፦
ዘርፉንም በልብሳችሁ ላይ አኑሩት እርሱንም በተመለከታችሁ ጊዜ የጌታን ትእዛዝ ሁሉ ታስታውሳላችሁ ታደርጉታላችሁም፥ ምኞታችሁንም በመከተል ያመነዘራችሁባትን የልባችሁንና የዐይኖቻችሁን ፈቃድ የማትከተሉ ትሆናላችሁ።
ጌታ አምላካችሁ ከእናንተ ጋር የገባውን ቃል ኪዳን እንዳትረሱ፥ ጌታ አምላካችሁም የከለከለውን በማናቸውም መልክ የተቀረጸውን ምስል እንዳታደርጉ ተጠንቀቁ።
“ብቻ አስተውል፥ ነፍስህንም በትጋት ጠብቅ፤ ዐይኖችህ ያዩትን ነገር እንዳትረሳ፥ በሕይወትህም ዘመን ሁሉ ከልብህ እንዳይለይ፥ ለልጆችህም ለልጅ ልጆችህም አሳውቃቸው።
እንደ ክርስቶስ ትምህርት ሳይሆን እንደ ሰው ወግና እንደ መሠረታዊው የዓለም ረቂቅ መንፈስ በፍልስፍናና በከንቱ መታለል ማንም እንዳይማርካችሁ ተጠንቀቁ።
ከግብጽ ምድር ያወጣቸውን የአባቶቻቸውን አምላክ ጌታን ተው፤ በዙሪያቸው ያሉት ሕዝቦች የሚያመልኩአቸውን አማልክት ተከተሉ፤ ሰገዱላቸውም፤ ጌታንም አስቈጡት፤