Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፀአት 13:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ሙሴም ሕዝቡን አለ፦ ከባርነት ቤት ከግብጽ የወጣችሁበትን ይህንን ቀን አስቡ፥ ጌታ ከዚህ ቦታ በብርቱ እጅ አውጥቶአችኋልና ስለዚህ የቦካ እንጀራ አትብሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ከዚያም ሙሴ ሕዝቡን እንዲህ አለ፤ “ከባርነት ምድር ከግብጽ የወጣችሁባትን ይህችን ዕለት አስታውሱ፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር በኀያል ክንዱ አውጥቷችኋል። እርሾ ያለበትን ማንኛውንም ነገር አትብሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ሙሴም ለሕዝቡ እንዲህ አለ፦ “ይህ ቀን በባርነት ስትገዙ የኖራችሁበትን የግብጽን ምድር ለቃችሁ የወጣችሁበት ስለ ሆነ ይህን ቀን አስታውሱ፤ እግዚአብሔር በታላቅ ኀይሉ በመታደግ ያወጣችሁ በዚህ ቀን ነው፤ ስለዚህ በዚህ ቀን እርሾ የነካው እንጀራ አትብሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ሙሴም ሕዝ​ቡን አለ፥ “ከባ​ር​ነት ቤት ከግ​ብፅ የወ​ጣ​ች​ሁ​ባ​ትን ይህ​ችን ቀን ዐስቡ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከዚህ ቦታ በበ​ረ​ታች እጅ አው​ጥ​ቶ​አ​ች​ኋ​ልና። ስለ​ዚህ የቦካ እን​ጀራ አት​ብሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ሙሴም ሕዝቡን አለ፥ “ከባርነት ቤት ከግብፅ የወጣችሁበትን ይህን ቀን አስቡ፤ እግዚአብሔር ከዚህ ቦታ በብርቱ እጅ አውጥቶአችኋልና፤ ስለዚህ የቦካ እንጀራ አትብሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፀአት 13:3
58 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አንተም በግብጽ ባርያ እንደ ነበርህና ጌታ እግዚአብሔር ከዚያ እንደ ተቤዠህ አስታውስ፤ ስለዚህ ይህን ታደርግ ዘንድ አዝዤሃለሁ።


አንተም በግብጽ ባርያ እንደ ነበርህ አስታውስ፥ ጌታ እግዚአብሔር በጸናች እጅና በተዘረጋ ክንድ ከዚያ አወጣህ፥ ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር የሰንበትን ቀን ትጠብቅ ዘንድ አዘዘህ።


“ከግብጽ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣሁህ ጌታ አምላክህ እኔ ነኝ።


አንተም በግብጽ ባርያ እንደ ነበርክ አስታውስ፤ ይህንንም ሥርዓት በጥንቃቄ ጠብቅ።


“ ‘ከግብጽ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣሁህ ጌታ አምላክህ እኔ ነኝ።


አንተም ራስህ በግብጽ ባርያ እንደ ነበርክና ጌታ እግዚአብሔር እንደ ተቤዠህ አስታውስ፤ ስለዚህ እኔ ዛሬ ይህን ነገር አዝሃለሁ።


በዚያን ጊዜ ከግብጽ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣህን ጌታ እንዳትረሳ ተጠንቀቅ።


የቦካውን ቂጣ ከእርሱ ጋር አትብላ፥ ከግብጽ አገር በችኮላ ስለ ወጣህ ከግብጽ አገር የወጣህበትን ቀን በዕድሜህ ሁሉ ታስብ ዘንድ ይህን ቂጣ፥ እርሱም የመከራን እንጀራ፥ ሰባት ቀን ከእርሱ ጋር ብላ።


ልብህ እንዳይታበይና፥ ከግብጽም ምድር ከባርነት ቤት ያወጣህን፥ ጌታን አምላክህን እንዳትረሳ፤


እንዲህም ይሆናል በሚመጣው ጊዜ ልጅህ፦ ይህ ምንድነው? ብሎ በጠየቀህ ጊዜ እንዲህ ትለዋለህ፦ ጌታ በብርቱ እጅ ከባርነት ቤት ከግብጽ አወጣን፤


እኛንና አባቶቻችንን ከባርነት ቤት ከግብጽ ምድር ያወጣን፥ በዓይናችንም ፊት እነዚያን ታላላቅ ተአምራት ያደረገ፥ በሄድንባትም መንገድ ሁሉ ባለፍንባቸውም አሕዛብ ሁሉ መካከል የጠበቀን፥ እርሱ ጌታ አምላካችን ነውና።


የባርነት ምድር ከሆነው ከግብጽ ካወጣህ ከጌታ ከእግዚአብሔር ሊያርቅህ ፈልጎአልና እስኪሞት ድረስ በድንጋይ ውገረው።


በግብጽ ባርያ እንደ ነበርህ አስታውስ፤ ስለዚህ ይህን ታደርግ ዘንድ አዝዤሃለሁ።”


ከግብጽ ምድር ስላወጣቸው ለጌታ የተጠበቀች ሌሊት ናት፤ ይህች ሌሊት በእስራኤል ልጆች ሁሉ ዘንድ በትውልዳቸው ሁሉ ለጌታ የተጠበቀች ናት።


ከግብጽ ባወጣችሁና ከባርነት ምድር በዋጃችሁ በአምላካችሁ በጌታ ላይ ሊያስታችሁ ተናግሮአልና፥ አምላካችሁ ጌታ እንድትከተሉት ካዘዛችሁ መንገድ እንድትመለሱ አድርጎአልና፥ ያ ነቢይ ወይም ሕልም አላሚ ይገደል፤ ስለዚህ ክፉውን ከመካከላችሁ አስወግዱ።”


ወይስ በፈተና፥ በተአምራት፥ በድንቅ፥ በጦርነት፥ በጸናች እጅና በተዘረጋ ክንድ፥ በሚያስፈራም ኃይል፥ በዐይናችሁ ፊት ጌታ አምላካችሁ እናንተን ከግብጽ ምድር እንዳወጣችሁ፥ አንድን ሕዝብ ከሌላ ሕዝብ መካከል ወስዶ የራሱ ሕዝብ ለማድረግ የሞከረ ሌላ አምላክ አለን?


የቂጣውን በዓል ጠብቅ፤ በተመደበው በአቢብ ወር ሰባት ቀን ያልቦካ ቂጣ እንዳዘዝሁህ ትበላለህ፤ በዚህ ወር ከግብጽ ምድር ወጥታችኋልና፥ በፊቴም ባዶ እጃችሁን አትታዩ።


“እንድትቀድሰው የሰንበትን ቀን አስታውስ።


ሰባት ቀን በቤታችሁ እርሾ አይገኝ፤ እርሾ ያለበትንም እንጀራ የሚበላ ነፍስ፥ ከመጻተኛው ጀምሮ እስከ አገሩ ተወላጅ ድረስ፥ ከእስራኤል ማኅበር ተለይቶ ይወገድ።


ሥጋውን በዚያች ሌሊት ይብሉ፤ በእሳት የተጠበሰውን ካልቦካ ቂጣና ከመራራ ቅጠል ጋር ይብሉት።


ጌታም ሙሴን አለው፦ “አሁን ፈርዖንን ምን እንደማደርገው ታያለህ በጸናች እጅ ይለቅቃቸዋል፥ በጸናችም እጅ ከምድሩ አስወጥቶ ይሰድዳቸዋል።”


እኔም እጄን እዘረጋለሁ፥ በማደርግባቸውም ተአምራቴ ሁሉ ግብጽን እመታለሁ፤ ከዚያም በኋላ ይለቅቃችኋል።


ሰባት ቀን ያልቦካ ቂጣ ትበላላችሁ፤ በመጀመሪያው ቀን ከቤቶቻችሁ እርሾ ታስወግዳላችሁ፤ ከመጀመሪያውም ቀን አንሥቶ እስከ ሰባተኛው ቀን የቦካ የሚበላ ያቺ ነፍስ ከእስራኤል ተለይታ ትጥፋ።


አገልጋዮቹ የአብርሃም ዘር፥ ለእርሱም የተመረጣችሁ የያዕቆብ ልጆች ሆይ፥ የሠራውን ድንቅ ሥር አስቡ፥ ተአምራቱን የተናገረውንም ፍርድ።


ለእኛ ለምናምነውም ከሁሉ በላይ ታላቅ የሆነውን፥ የኀይሉ ታላቅ ብርታት አሠራር፥ ኀይሉን ምን እንደሆን እንድታውቁ፥


አመሰገነ ቆርሶም “እንካችሁ ብሉ፤ ይህ ስለ እናንተ የሚሆን ሥጋዬ ነው፤ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት፤” አለ።


ስለዚህ ተንኰልና ክፋት በሞላበት በአሮጌ እርሾ ሳይሆን እርሾ በሌለበት የቅንነትና የእውነት ቂጣ በዓላችንን እናክብር።


ኅብስትንም አንሥቶ፥ አመስግኖ፥ ቆረሰና እንዲህ ሲል ሰጣቸው፦ “ይህ ስለ እናንተ የሚሰጠው ሥጋዬ ነው፤ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት”።


በፈርዖን፥ በአገልጋዮቹ ሁሉና በምድሩ ሕዝብ ሁሉ ላይ ምልክትና ተአምራት አሳየህ፤ በእነርሱ ላይ መታበያቸውን አውቀህ ነበርና፥ እስከ ዛሬም እንዳለው ለራስህ ስምን ሠራህ።


ተአምራቱንም የተናገረውንም ፍርድ፥ የሠራትን ድንቅ አስቡ፤ እናንተ


ወደ ቤቱም ስትገቡ ሰላምታ ስጡ፤


ስለዚህም ለእስራኤል ልጆች እንዲህ በላቸው፦ ‘እኔ ጌታ ነኝ፥ ከግብፃውያን ጭቆና አወጣችኋለሁ፥ ከተገዥነታችሁም አላቅቃችኋለሁ፤ በተዘረጋች ክንድ በታላቅ የፍርድ ሥራም አድናችኋለሁ፤


ፈርዖንም እናንተን አይሰማችሁም፥ እጄንም በግብጽ ላይ አደርጋለሁ፥ ሠራዊቴን፥ ሕዝቤን የእስራኤልን ልጆች፥ በታላቅ የፍርድ ሥራ ከግብጽ ምድር አወጣለሁ።


በዚህም ቀን ሠራዊታችሁን ከግብጽ ምድር አውጥቼአለሁና የቂጣውን በዓል ጠብቁት፤ እንግዲህ ይህን ቀን በትውልዳችሁ ለዘለዓለም ሥርዓት ትጠብቃላችሁ።


በእጅህ እንደ ምልክት በዐይኖችህም መካከል እንደ መታሰቢያ ይሁንልህ፥ የጌታ ሕግ በአፍህ እንዲሆን፥ ጌታ በብርቱ እጅ ከግብጽ አውጥቶሃልና።


ነገር ግን ጌታ ስለ ወደዳችሁ፥ አባቶቻችሁም የማለላቸውን መሐላ ስለ ጠበቀ፥ ስለዚህ እግዚአብሔር በጽኑ እጅ አወጣችሁ፥ ከባርነትም ቤት ከግብጽ ንጉሥ ከፈርዖን እጅ አወጣችሁ።


ሰዎች ከሩቅ የሚመጡት ስለ ታላቁ ስምህ፥ ስለ ጠንካራዪቱ እጅህ፥ ስለ ተዘረጋችው ክንድህ ሰምተው ነውና፤ እንግዳው መጥቶ ወደዚህ ቤተ መቅደስ ቢጸልይ፥


ሃሌ ሉያ! እስራኤል ከግብጽ፥ የያዕቆብም ቤት ከእንግዳ ሕዝብ በወጣ ጊዜ፥


እስራኤልንም ከመካከላቸው ያወጣውን፥ ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና፥


በአራተኛው ትውልድ ግን ወደዚህ ይመለሳሉ፥ የአሞራውያን ኃጢአት ገና አልተፈጸመምና።”


ለእኔ ሕዝብ አድርጌ እቀበላችኋለሁ፥ አምላክም እሆናችኋለሁ፤ እኔም ከግብጽ ጭቆና ያወጣኋችሁ ጌታ አምላካችሁ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ።


“ይህ ወር የወሮች መጀመሪያ ይሁናችሁ፤ ከዓመቱ ወሮችም የመጀመሪያ ይሁናችሁ።


እንዲህም ሆነ አራት መቶ ሠላሳ ዓመት ከተፈጸመ በኋላ በዚህ ቀን የጌታ ሠራዊት ሁሉ ከግብጽ ምድር ወጡ።


“የቂጣውን በዓል ጠብቀው፤ በአቢብ ወር ከግብጽ ወጥተሃልና በተወሰነው ጊዜ በአቢብ ወር እንዳዘዝሁህ ሰባት ቀን ቂጣ ብላ።


አንተም ልጅህን እንዲህ ትለዋለህ፥ ‘በግብጽ የፈርዖን ባርያዎች ነበርን፤ ጌታም በጽኑ እጅ ከግብጽ አወጣን፥


“ከዚያም ጌታ፥ ‘ተነሥ፥ ከዚህ ፈጥነህ ውረድ፥ ከግብጽ ያወጣሃቸው ሕዝብህ ክፉ ነገር በማድረግ ረክሰዋል፤ ፈጥነው ካዘዝኋቸው መንገድ ፈቀቅ ብለዋል፤ ቀልጦ የተሠራ ምስልም ለራሳቸው ሠርተዋል’ አለኝ።


“የአባትህ፥ ወይም የእናትህ ልጅ ወንድምህ፥ ወንድ ልጅህ፥ ወይም ሴት ልጅህ ወይም የምትወዳት ሚስትህ ወይም የቅርብ ወዳጅህ አንዳቸው ቢሆኑ በምሥጢር ሊያስትህ ቢሞክር፥


ከዚያም እስራኤል ሁሉ ሰምተው ይፈራሉ፤ ከመካከልህም በማንም እንደዚህ ያለውን ክፉ ነገር ዳግም አይደረግም።”


“አምላክህ ጌታ በአቢብ ወር ከግብጽ በሌሊት ስላወጣህ፥ የአቢብን ወር ጠብቅ፤ የአምላክህን የጌታ ፋሲካ አክብርበት።


ከዚያም በብርቱ እጅና በተዘረጋች ክንድ፥ በታላቅ ድንጋጤ፥ በተአምራትና በድንቅም ጌታ ከግብጽ አወጣን።


ከግብጽ ምድር ያወጣቸውን የአባቶቻቸውን አምላክ ጌታን ተው፤ በዙሪያቸው ያሉት ሕዝቦች የሚያመልኩአቸውን አማልክት ተከተሉ፤ ሰገዱላቸውም፤ ጌታንም አስቈጡት፤


ጌታ አንድ ነቢይ ላከላቸው፤ እርሱም እንዲህ አለ፤ “የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል ከባርነት ቤት ከግብጽ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ ነኝ።


እነዚህም በታላቁ ኃይልህና በብርቱ እጅህ የተቤዠሃቸው ባርያዎችህና ሕዝብህ ናቸው።


ኃያል ክንድ አለህ፥ እጅህ በረታች ቀኝህም ከፍ ከፍ አለች።


በጸናች እጅ በተዘረጋችም ክንድ፥ ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና፥


“የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ አባቶቻችሁን ከባርነት ቤት ከግብጽ አገር ባወጣኋቸው ቀን ከእነርሱ ጋር እንዲህ ብዬ ቃል ኪዳን አደረግሁ፦


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች