ምሳሌ 1:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደምን ለማፍሰስ “ና እናድባ፥ ለንጹሕም ያለ ምክንያት ወጥመድን እንሸምቅበት” ቢሉ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ከእኛ ጋራ ናና፣ ደም ለማፍሰስ እናድባ፤ በደል በሌለበት ሰው ላይ እንሸምቅ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምናልባትም እንዲህ ይሉህ ይሆናል፦ “ከበደል ንጹሕ የሆነውን ሰው መንገድ ላይ አድብተን እንድንገድለው ከእኛ ጋር ና! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ና ከእኛ ጋር ደምን በማፍሰስ አንድ ሁን፥ ጻድቅ ሰውንም በምድር እንቅበር፥ ብለው ቢማልዱህ፥ |
እኔም ለመታረድ እንደሚነዳ እንደ የዋህ በግ ጠቦት ሆንሁ፤ እነርሱም፦ “ዛፉን ከነፍሬው እናጥፋ፥ ስሙም ከእንግዲህ ወዲህ እንዳይታወስ ከሕያዋን ምድር እናስወግደው” ብለው ምክርን እንዳሰቡብኝ አላወቅሁም ነበር።
እንግዲህ አሁን እናንተ ከሸንጎው ጋር ሆናችሁ ስለ እርሱ አጥብቃችሁ እንደምትመረምሩ መስላችሁ ወደ እናንተ እንዲያወርደው ለሻለቃው አመልክቱት፤ እኛም ሳይቀርብ እንድንገድለው የተዘጋጀን ነን፤” አሉአቸው።