Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 5:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 በሕዝቤ መካከል ክፉዎች ሰዎች ተገኝተዋል፤ እንደ ወፍ አጥማጆችም ያደባሉ፥ ወጥመድንም ይዘረጋሉ ሰዎችንም ያጠምዳሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 “በሕዝቤ መካከል ክፉ ሰዎች አሉና፤ ወፍ እንደሚያጠምዱ ሰዎች፣ ወጥመድ ዘርግተው ሰው እንደሚይዙ ሰዎችም ያደባሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 “በሕዝቤ መካከል የሚኖሩ ክፉ ሰዎች አሉ፤ እነርሱም ወፎችን በወጥመድ እንደሚይዝ ሰው ናቸው፤ ስለዚህ ሰዎችን ለማጥመድ መረባቸውን ዘርግተው ያደባሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 በሕ​ዝቤ መካ​ከል ክፉ​ዎች ሰዎች ተገ​ኝ​ተ​ዋል፤ ሰዎ​ች​ንም ይዘው ይገ​ድሉ ዘንድ ወጥ​መ​ድን ይዘ​ረ​ጋሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 በሕዝቤ መካከል ክፉዎች ሰዎች ተገኝተዋል፥ እንደ አጥማጆችም ያደባሉ፥ ወጥመድንም ይዘረጋሉ ሰዎችንም ያጠምዳሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 5:26
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ንጹሕንም በስውር ለመንደፍ ቀስትን ገተሩ፥ ድንገት ይነድፉታል አይፈሩምም።


ደምን ለማፍሰስ “ና እናድባ፥ ለንጹሕም ያለ ምክንያት ወጥመድን እንሸምቅበት” ቢሉ፥


የሸንጋይ ሽንገላ ክፉ ናት፤ የችግረኛም አቤቱታ ትክክል ቢሆንም እንኳን በሐሰት ቃል ድሀውን ለማጥፋት ክፉን አሳብ ያስባል።


በኃይልህ ጩኽ፥ አትቈጥብ፥ ድምፅህን እንደ መለከት አንሣ፥ ለሕዝቤ መተላለፋቸውን ለያዕቆብ ቤትም ኃጢአታቸውን ንገር።


ለነፍሴ ጉድጓድ ቈፍረዋልና በውኑ በመልካም ፋንታ ክፉ ይመለሳልን? ስለ እነርሱ በመልካም ለመናገር ቁጣህንም ከእነርሱ ለመመለስ በፊትህ እንደ ቆምሁ አስታውስ።


ሊይዙኝ ጉድጓድ ቆፍረዋልና፥ ለእግሮቼም ወጥመድ ሸሽገዋልና ድንገት በላያቸው ጭፍራ ባመጣህ ጊዜ ከቤታቸው ጩኸት ይሰማ።


“ሕዝቤ ሰንፈዋልና አላወቁኝም፤ ሰነፎች ልጆች ናቸው፥ ማስተዋልም የላቸውም፤ ክፉ ነገርን ለማድረግ ብልሃተኞች ናቸው፥ በጎ ነገርን ማድረግ ግን አያውቁም።”


ምላሳቸው የተሳለ ፍላጻ ነው፤ ሽንገላን ይናገራሉ፤ ሰው ከባልንጀራው ጋር በሰላም ይናገራል፥ በልቡ ግን ያደባበታል።


በክፉ ቤት የክፋት መዝገብ፥ አስጸያፊ ሐሰተኛ መስፈሪያ አሁንም አለን?


ታማኝ ሰው ከምድሪቱ ጠፍቶአል፥ በሰው መካከል ቅን የለም፤ ሁሉም ለደም ያደባሉ፥ እያንዳንዱም ወንድሙን በመረብ ያጠምዳል።


እንዲሁም ደግሞ የስምዖን ወዳጆች የነበሩ የዘብዴዎስ ልጆች ያዕቆብና ዮሐንስም ተደነቁ። ኢየሱስም ስምዖንን፦ “አትፍራ፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሰዎችን የምታጠምድ ትሆናለህ፤” አለው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች