Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 11:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 እኔም ለመታረድ እንደሚነዳ እንደ የዋህ በግ ጠቦት ሆንሁ፤ እነርሱም፦ “ዛፉን ከነፍሬው እናጥፋ፥ ስሙም ከእንግዲህ ወዲህ እንዳይታወስ ከሕያዋን ምድር እናስወግደው” ብለው ምክርን እንዳሰቡብኝ አላወቅሁም ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 እኔም ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት ነበርሁ፤ እነርሱም፣ “ዛፉን ከፍሬው ጋራ እንቍረጥ፤ ከሕያዋን ምድር እናጥፋው፤ ከእንግዲህም ወዲያ ስሙ አይታሰብ” ብለው እንዳደሙብኝ ዐላወቅሁም ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ወደ ዕርድ እንደሚሄድ የበግ ጠቦት ሆኜ ነበር፤ እነርሱ “ስሙ ዳግመኛ እንዳይታወስ ዛፉን ከነፍሬው እናጥፋ፤ ከሕያዋያን ዓለም እናስወግደው” ብለው በእኔ ላይ ማደማቸውን አላወቅሁም ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 እኔም ለመ​ታ​ረድ እን​ደ​ሚ​ነዳ እንደ የዋህ ጠቦት በግ ሆንሁ፤ እነ​ር​ሱም በእ​ን​ጀ​ራው ዕን​ጨት እን​ጨ​ምር ስሙም ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ እን​ዳ​ይ​ታ​ሰብ ከሕ​ያ​ዋን ምድር እና​ጥ​ፋው ብለው ክፉ ምክ​ርን እን​ዳ​ሰ​ቡ​ብኝ አላ​ወ​ቅ​ሁም ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 እኔም ለመታረድ እንደሚነዳ እንደ የዋህ በግ ጠቦት ሆንሁ፥ እነርሱም፦ ዛፉን ከፍሬው ጋር እንቍረጥ፥ ስሙም ከእንግዲህ ወዲህ እንዳይታሰብ ከሕያዋን ምድር እናጥፋው ብለው ምክርን እንዳሰቡብኝ አላወቅሁም ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 11:19
28 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሰው መንገድዋን አያውቅም፥ በሕያዋን አገር አትገኝም።


ተተኪ አይኑረው፥ በቀጣይ ትውልድ ስማቸው ይደምሰስ።


ለዘለዓለም አይናወጥም፥ የጻድቅ መታሰቢያ ለዘለዓለም ይኖራል።


በሕያዋን አገር በጌታ ፊት እሄዳለሁ።


ወደ ቀኝ ተመለከትሁ አየሁም፥ የሚያውቀኝም አጣሁ፥ መሸሸጊያም የለኝም፥ ስለ ነፍሴም የሚያስብ የለም።


የጌታን ቸርነት በሕያዋን ምድር እንደማይ አምናለሁ።


እንደ ሞተ ሰው ከልብ ተረሳሁ፥ እንደ ተበላሸ ዕቃም ሆንሁ።


በእኔ ላይ ተሰበሰቡ ደስም አላቸው፥ ግፈኞች በእኔ ላይ ተሰበሰቡ እኔም አላወቅሁም፥ መቦጫጨቃቸውን አላቆሙም።


ከመልካም ይልቅ ክፋትን፥ ጽድቅንም ከመናገር ይልቅ ዓመፃን ወደድህ።


ሕዝብህን በምክር ሸነገሉአቸው፥ በቅዱሳንህም ላይ ተማከሩ።


የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው፥ የክፉ ስም ግን ይጠፋል።


እንደ ክፉ ሰው በጻድቅ ቤት ላይ አትሸምቅ፥ ማደሪያውንም አታውክ።


እርሱ እንዲህ ስቶ ይከተላታል፥ በሬ ለመታረድ እንደሚነዳ፥ አጋዘን ቸኩሎ ወደ ወጥመድ እንደሚገባ፥


የሸንጋይ ሽንገላ ክፉ ናት፤ የችግረኛም አቤቱታ ትክክል ቢሆንም እንኳን በሐሰት ቃል ድሀውን ለማጥፋት ክፉን አሳብ ያስባል።


ደግሞም፦ በሕያዋን ምድር ጌታን አላይም፤ በዓለምም የሚኖሩትን ሰዎች ከእንግዲህ አልመለከትም አልኩ።


ከአንተም ጋር ይዋጋሉ፥ ነገር ግን አንተን ላድንህ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና ድል አይነሡህም፥ ይላል ጌታ።”


እነርሱም፦ “ሕግ ከካህን፥ ምክርም ከጠቢብ፥ ቃልም ከነቢይ አይጠፋምና ኑ፥ በኤርምያስ ላይ ሤራን እናሢር። ኑ፥ በአንደበት እንምታው፥ ቃላቱንም ሁሉ አናድምጥ” አሉ።


የብዙ ሰዎችን የክፋት ሹክሹክታ ሰምቻለሁ፥ ማስፈራራትም ከብቦኛል። መውደቄን የሚጠብቁ የሰላሜ ሰዎች ሁሉ፦ “ምናልባት ይታለል እንደሆነ፥ እናሸንፈውም እንደሆነ፥ እርሱንም እንበቀል እንደሆነ፥ ክሰሱት እኛም እንከስሰዋለን” ይላሉ።


ኤርምያስም ለሕዝቡ ሁሉ እንዲናገር ጌታ ያዘዘውን ነገር ሁሉ ተናግሮ በፈጸመ ጊዜ፥ ካህናትና ነቢያት ሕዝቡም ሁሉ፦ “ፈጽሞ ትሞታለህ።


በቀላቸውን ሁሉና በእኔ ላይ ያለውን አሳባቸውን ሁሉ አየህ።


ኤላምም በዚያ አለች ብዛትዋም ሁሉ በመቃብሯ ዙሪያ ነው፤ በሕያዋን ምድር ያሸበሩ ሁሉ በሰይፍ ወድቀው ተገድለዋል ሳይገረዙም ወደ ታችኛው ምድር ወርደዋል፥ ወደ ጉድጓድም ከሚወርዱ ጋር እፍረታቸውን ተሸክመዋል።


ነቢዩ ከአምላኬ ጋር በኤፍሬም ላይ ጠባቂ ነው፤ አሁን ግን በመንገዱ ሁሉ ላይ የወፍ ወጥመድ፥ በአምላኩም ቤት ጥላቻ አለ።


ከጋድ የደዑኤል ልጅ ኤሊሳፍ፥


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች