Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘኍል 33:4 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 በዚያም ጊዜ ግብፃውያን እግዚአብሔር የገደላቸውን በኵሮቻቸውን ይቀብሩ ነበር፤ በአማልክቶቻቸውም ደግሞ እግዚአብሔር ፈረደባቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 በዚህ ጊዜ ግብጻውያን እግዚአብሔር ከመካከላቸው የገደለባቸውን በኵሮቻቸውን ይቀብሩ ነበር፤ እግዚአብሔር በግብጽ አማልክት ላይ ፈርዶ ነበርና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 በዚያም ጊዜ ግብፃውያን ጌታ የገደላቸውን በኩሮቻቸውን ሁሉ ይቀብሩ ነበር፤ በአማልክቶቻቸውም ላይ ደግሞ ጌታ ፈረደባቸው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ግብጻውያን በዚያን ጊዜ በእግዚአብሔር መቅሠፍት የሞቱትን የበኲር ልጆቻቸውን ይቀብሩ ነበር፤ እግዚአብሔርም በአማልክታቸው ላይ እንኳ ፈርዶአል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 በዚ​ያም ጊዜ ግብ​ፃ​ው​ያን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የገ​ደ​ላ​ቸ​ውን በኵ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን ይቀ​ብሩ ነበር፤ በአ​ማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ደግሞ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፈረ​ደ​ባ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 33:4
8 Referencias Cruzadas  

እርሱ የእግዚአብሔር ፋሲካ ነው። እኔም በዚያች ሌሊት በግብፅ አገር አልፋለሁ፤ በግብፅም አገር ከሰው እስከ እንስሳ ድረስ በኵርን ሁሉ እገድላለሁ፤ በግብፅም አማልክት ሁሉ ላይ እፈርድባቸዋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።


ትዕቢት ባደረጉባቸው ነገር እግዚአብሔር ከአማልክት ሁሉ እንዲበልጥ አሁን አወቅሁ አለ።


ስለ ግብጽ የተነገረ ሸክም። እነሆ፥ እግዚአብሔር በፈጣን ደመና እየበረረ ወደ ግብጽ ይመጣል፥ የግብጽም ጣዖታት በፊቱ ይርዳሉ፥ የግብፅም ልብ በውስጥዋ ይቀልጣል።


እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ የተፈራ ይሆናል፥ የምድርንም አማልክት ሁሉ ያከሳቸዋል፥ በአሕዛብም ደሴቶች ሁሉ ላይ የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ በስፍራቸው ሆነው ለእርሱ ይሰግዳሉ።


በኵር ሁሉ ለእኔ ነውና ሌዋውያን ለእኔ ይሁኑ፤ በግብፅ ምድር በኵርን ሁሉ በመታሁ ቀን፥ ከእስራኤል ዘንድ በኵርን ሁሉ በመታሁ ቀን፥ ከእስራኤል ዘንድ በኵርን ሁሉ፥ ሰውንና እንስሳን፥ ለእኔ ለይቼአለሁ፤ ለእኔ ይሁኑ። እኔ እግዚአብሔር ነኝ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos