ኤልሳዕም፥ “አቤቱ፥ ያይ ዘንድ ዐይኖቹን፥ እባክህ፥ ግለጥ” ብሎ ጸለየ። እግዚአብሔርም የብላቴናውን ዐይኖች ገለጠ፤ እነሆም፥ የእሳት ፈረሶችና ሰረገሎች በኤልሳዕ ዙሪያ ተራራውን ሞልተውት አየ።
ዘካርያስ 6:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ተመልሼም ዓይኖቼን አነሣሁ፥ እነሆም፥ አራት ሰረገሎች ከሁለት ተራራ መካከል ሲወጡ አየሁ፣ ተራሮቹም የናስ ተራሮች ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንደ ገናም ወደ ላይ ተመለከትሁ፤ እነሆ አራት ሠረገሎች ከሁለት ተራራ መካከል ሲወጡ አየሁ፤ ተራሮቹም የናስ ተራሮች ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ተመልሼም ዐይኖቼን አነሣሁ፥ እነሆም፥ አራት ሰረገሎች ከሁለት ተራራ መካከል ሲወጡ አየሁ፤ ተራሮቹም የናስ ተራሮች ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሌላም ራእይ አራት ሠረገሎች ከሁለት የነሐስ ተራራዎች መካከል ሲወጡ አየሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ተመልሼም ዓይኖቼን አነሣሁ፥ እነሆም፥ አራት ሰረገሎች ከሁለት ተራራ መካከል ሲወጡ አየሁ፥ ተራሮቹም የናስ ተራሮች ነበሩ። |
ኤልሳዕም፥ “አቤቱ፥ ያይ ዘንድ ዐይኖቹን፥ እባክህ፥ ግለጥ” ብሎ ጸለየ። እግዚአብሔርም የብላቴናውን ዐይኖች ገለጠ፤ እነሆም፥ የእሳት ፈረሶችና ሰረገሎች በኤልሳዕ ዙሪያ ተራራውን ሞልተውት አየ።
እነሆ፥ እግዚአብሔር መዓቱን በቍጣ፥ ዘለፋውንም በእሳት ነበልባል ይመልስ ዘንድ እንደ እሳት ይመጣል፤ ሰረገሎቹም እንደ ዐውሎ ነፋስ ይሆናሉ።
እነሆ! እንደ ደመና ይወጣል፤ ሰረገሎቹም እንደ ዐውሎ ነፋስ ናቸው፤ ፈረሶቹም ከንስር ይልቅ ፈጣኖች ናቸው። ተዋርደናልና ወዮልን።
ችግረኛውን ከመሬት ያነሣዋል፤ ምስኪኑንም ከጕድፍ ያነሣዋል፤ ከሕዝቡ መኳንንት ጋር ያስቀምጠው ዘንድ፥ የክብርንም ዙፋን ያወርሰው ዘንድ።