ዘካርያስ 5:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዓይኖቼንም አንሥቼ አየሁ፥ እነሆም፥ ሁለት ሴቶች ወጡ፥ ነፋስም በክንፎቻቸው ነበረ፣ ክንፎቻቸውም እንደ ሽመላ ክንፎች ነበሩ፣ የኢፍ መስፈሪያውንም በምድርና በሰማይ መካከል አነሡት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ወደ ላይ ተመለከትሁ፤ እነሆም፣ ከፊቴ ሁለት ሴቶች ነበሩ፤ በክንፎቻቸውም ነፋስ ነበር፤ ክንፎቻቸውም እንደ ሽመላ ክንፎች ነበሩ፤ የኢፍ መስፈሪያውንም በምድርና በሰማይ መካከል አነሡት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ዐይኖቼን አንሥቼ አየሁ፥ እነሆም፥ ሁለት ሴቶች ወጡ፥ በክንፎቻቸውም ነፋስ ነበረ፤ ክንፎቻቸውም እንደ ሽመላ ክንፎች ነበሩ፤ የኢፍ መስፈሪያውንም በምድርና በሰማይ መካከል አነሡት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀና ብዬ ስመለከት እነሆ ሁለት ሴቶች እየበረሩ ወደ እኔ መጡ፤ ክንፎቻቸውም እንደ ሽመላ ክንፎች ብርቱዎች ነበሩ። እነርሱም ያንን ቅርጫት ከመሬት አንሥተው ወደ ሰማይ ይዘውት በረሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዓይኖቼንም አንሥቼ አየሁ፥ እነሆም፥ ሁለት ሴቶች ወጡ፥ ነፋስም በክንፎቻቸው ነበረ፥ ክንፎቻቸውም እንደ ሽመላ ክንፎች ነበሩ፥ የኢፍ መስፈሪያውንም በምድርና በሰማይ መካከል አነሡት። |
ሽመላ በሰማይ ጊዜዋን አውቃለች፤ ዋኖስና ጨረባ፥ ዋሊያም የመምጣታቸውን ጊዜ ይጠብቃሉ፤ ሕዝቤ ግን የእግዚአብሔርን ፍርድ አላወቁም።
በብብታቸው እንደ መሬት፤ በእግዚአብሔርም ቤት እንደ ንስር ይመጣል። ቃል ኪዳኔን ተላልፈዋልና፥ በሕጌም ላይ ዐምፀዋልና።