ዘካርያስ 5:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም፦ ይህች ክፋት ናት አለኝ፣ በኢፍ መስፈሪያው ውስጥ ጣላት፥ የእርሳሱንም ጠገራ በመስፈሪያ አፍ ላይ ጣለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም፣ “ይህች ርኩሰት ናት” ብሎ ወደ ኢፍ መስፈሪያ መልሶ አስገባት፤ የእርሳሱንም ክዳን ወደ ቅርጫቱ አፍ ገፍቶ ገጠመው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም፦ “ይህች ክፋት ናት” አለኝ፤ ከዚያም በኢፍ መስፈሪያው ውስጥ ጣላት፥ የእርሳሱንም ጠገራ በመስፈሪያ አፍ ላይ ጣለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መልአኩም “እነሆ ይህች ሴት የዐመፅ ምሳሌ ነች” ከአለኝ በኋላ ወደ ታች ገፍቶ ወደ ቅርጫቱ ውስጥ አስገባት፤ ክዳኑንም መልሶ ገጠመው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም፦ ይህች ክፋት ናት አለኝ፥ በኢፍ መስፈሪያው ውስጥ ጣላት፥ የእርሳሱንም ጠገራ በመስፈሪያ አፍ ላይ ጣለ። |
ኖን። በእጄ ስለተታቱ ኀጢአቶች ተጋ፤ በአንገቴ ላይ ወጥተዋል፤ ጕልበቴ ደከመ። እግዚአብሔር ልቋቋመው በማልችለው መከራ እጅ ሰጥቶኛልና።
“እህልን እንሸጥ ዘንድ መባቻው መቼ ያልፋል? የኢፍ መስፈሪያውንም እያሳነስን፥ ሰቅሉንም እያበዛን፥ በሐሰተኛም ሚዛን እያታለልን፥