እንግዶችን ስለ መቀበል እጅግ የተጠላ ጠባይን ወድደዋልና፥ እነዚህ የማያውቋቸው በደረሱ ጊዜ አልተቀበሉአቸውም፤ እነዚያ ግን መልካም እያደረጉ ሲጠቅሙአቸው በእነርሱ ዘንድ በእንግድነት የኖሩትን አስጨንቀው ገዙአቸው።
ከአሸባሪው ነጐድጓዳዊ ማስጠንቀቂያ በኋላ፥ ቅጣቱ በኃጢአተኞቹ ላይ ዘነበ። በመጻተኞች ላይ ላሳዩትም ጥላቻ የወንጀሎቻቸውን ዋጋ አገኙ።