የጻድቃን ልጆችን ይገድሉ ዘንድ ባሰቡና በመከሩ ጊዜ፥ ለዘለፋ ሊሆንባቸው አንዱ ሕፃን ተጥሎ ዳነ። በእርሱም ብዙዎች ልጆቻቸውንና ማኅበራቸውን ሁሉ ያለ ርኅራኄ በብዙ ውኃ አጠፋህ።
የቅዱሳኑ ልጆች የሆኑትን ሕፃናት ለመግደል እነርሱ እንደወሰኑ፥ ለአደጋ ከተጋለጡትም መሀል አንድ ልጅ ብቻ እንደተረፈው ሁሉ፥ አንተም ልጆቻቸውን በሙሉ ውሃው፥ ማዕበሉም እንዲያጠፋቸው አደረግህ።