ዝንጉዎች እንዲክዱህ ባወቅህ ጊዜ በክንድህ ኀይል ተቀሠፉ፤ በልዩ ዝናምና በረድ፥ ያለ ምሕረትና ያለ መገታት በወረደ በሰማይ ሿሿቴ ጠፉ፥ በእሳትም አለቁ።
አንተን አናውቅም ያሉ ከሐዲዎች፥ በጠንካራው ክንድህ ተመቱ፤ ያልተለመደ ዝናብና በረዶ ወረደባቸው፤ የማያባራ ዶፍ አጥለቀለቃቸው፤ እሳትም በላቸው።