መጽሐፈ ጥበብ 15:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሸክላ ሠሪ ለስላሳ አፈርን በለወሰ ጊዜ ከእኛ ለእያንዳንዱ ሁሉ ሊያገለግል የሚገባውን የተለያየ ሥራን ይሠራል፥ ነገር ግን ከዚያው ጭቃ ለንጹሕ ሥራ አገልግሎት ዕቃዎችን ይሠራል፥ እንደዚሁም ለሌሎች ሥራዎች በእነዚህ አምሳል ይሠራል፤ የእነዚህም ሁሉ ተግባር ለተለያየ መፍቅድ ነው፥ ነገር ግን ይህ ወይም ያ ለምን ጥቅም እንደሚውል ፈራጁ ዳኛ ሸክላ ሠሪው ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሸክላ ሠሪው ለስላሳውን አፈር ለውሶ፥ ቀርጾና ደክሞ እኛ የምንገለገልባቸውን ቁሳቁሶች ይሠራል፤ ለከበረ ዓላማ የሚውለውን ዕቃ ለረከሰውም ቢሆን እንዲሁ የሚሠራው ከዚያው ጭቃ ነው። ከሁለቱ ግልጋሎቶች የትኛው ለየትኛው እንደሚውልም የሚወስነው እርሱ ነው። |