ሰነፍን ሰው፥ አእምሮ የሌለውንም ሰው፥ በእርጅናውም ወደ ዝሙት የሚሄድ ሽማግሌን ስለ መምከር አትፈር፤ ስለዚህ በሰው ሁሉ ዘንድ በእውነት ብልህና ዐዋቂ ትሆናለህ።
አላዋቂውንና ሞኙን ሰው፥ ከወጣቶች ጋር የሚዳራውን ያረጀ ሽማግሌ፥ ለማረም አትፈር፤ በውል የተማርክ መሆንህን ያኔ ታሳያለህ፤ ሰውም ሁሉ ይህንኑ ያረጋግጥልሃል።