Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


Este libro no es inspirado por Dios y no forma parte del canon cristiano ni del Tanaj judío. Se muestra solo con fines históricos y de estudio. Ver explicación completa

መጽሐፈ ሲራክ 42 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 በሚከተሉት ሁናቴዎች ልታፍር አይገባህም፤ ሌሎች በሚያስቡትን በመፍራት፥

2 በልዑል እግዚአብሔር ሕግ ወይም በቃል ኪዳኑ፥ ከሐዲውን በነጻ በሚያሰናብት ፍርድ፥

3 ከመንገድ ጓደኛህ ጋር በመተሳሰብህ፥ ሀብትህን ወዳጆችህ በማካፈልህ፥

4 በሚዛኑና በክብደቱ ትክክለኛነት ጥቂት ወይም ብዙ በማትረፍህ፥

5 በንግድ ሥራ በመጠቀምህ፥ ልጆችህን በሚገባ በመቅጣትህ፥ አመፀኛውን አገልጋይ እስኪደማ በመግረፍህ፥ በኃጢአት አትውደቅ።

6 ሚስትህ ሁሉን ማወቅ የምትሻ ከሆነ፥ ማሸጊያህን መጠቀም ያስፈልጋል፤ በርካታ እጆች ባሉበትም ንብረትህን ቆልፍ።

7 ከዕቃ ቤት የሚወጣው ሁሉ በቁጥጥርና በሚዛን ይሁን፤ ወጪዎችና ገቢዎች ጽሑፍ ይመዝገቡ።

8 አላዋቂውንና ሞኙን ሰው፥ ከወጣቶች ጋር የሚዳራውን ያረጀ ሽማግሌ፥ ለማረም አትፈር፤ በውል የተማርክ መሆንህን ያኔ ታሳያለህ፤ ሰውም ሁሉ ይህንኑ ያረጋግጥልሃል።


አባት ስለ ሴት ልጁ ያለበት ጭንቅ

9 እርሷ ባታውቀውም፥ የሴት ልጅ አባት እንቅልፍ የለውም፤ ስለ እርሷ ሲያስብ እንቅልፉን ያጣል በወጣትነቷ ቆማ ብትቀር፥ ካገባች በኋላ ባሏ ቢጠላት፥

10 በልጃረገድነቷ ብትደፈር፥ ባባቷም ቤት ብትወልድ፥ ባል ኖሯት ብትማግጥ፥ ከጋብቻ በኋላ ብትመነኩስ በማለት ይጨነቃል።

11 ልጅህ አስቸጋሪ ነችን? የጠላቶችህ መሳቂያ፥ የከተማው መዘባበቻ፥ የወሬኞች መጠቋቆሚያ እንዳታደርግህ፥ በሕዝብም ፊት ኀፍረትን እንዳታከናንብህ በብርቱ ጠብቃት።


ሴቶች

12 ስለ ቁንጅናው ብላችሁ ወንድ አትመልከቱ፤ ከሴቶችም ጋር አትቀመጡ፥

13 ብል ከልብስ እንደሚመጣ፥ የሴት ክፋትም የሚመነጨው እንዲሁ ከሴት ነው።

14 ከሴት ደግነት የወንድ ክፋት ይሻላል፤ ሴቶች ኀፍረትንና ጥላቻን ያመጣሉ።


የእግዚአብሔር ታላቅነት ሀ. በተፈጥሮ ውስጥ

15 የእግዚአብሔርን ሥራዎች ቀጥዬ አስታውሳችኋለሁ፤ ያየሁትንም እዘረዝራለሁ። በእግዚአብሔር ቃል ሥራዎች ሁሉ ሕያው ሆኑ፤ ፍጥረታትም ሁሉ ፈቃድን ይፈጽማሉ።

16 የምታበራዋ ፀሐይ ሁሉንም ዘቅዝቃ ትመለከታለች፤ የእግዚአብሔርም ሥራ በክብሩ የተመላ ነው።

17 እግዚአብሔር ድንቅ ሥራዎቹን ይገልጽ ዘንድ፤ ለቅዱሳኑ ሥልጣንን አልሰጠም፤ ኃያሉ እግዚአብሔር ሥራዎቹን ሁሉ አጽንቶ ፈጥሯል፤ ዓለምንም በክብሩ ፊት አቁሟል።

18 ጥልቁን ጉድጓድ፥ የሰውንም ልብ ይመረምራል፤ አሳሳች መንገዶቻቸውንም ይመለከታል። ልዑል እግዚአብሔር ሁሉንም ያውቃል፤ የዘመናትንም ምልክቶች ያስተውለልና።

19 ያለፈውንም፥ የሚመጣውንም ይናገራል፤ የሚሥጢራትንም አካሄድ ይገለጻል።

20 አንዲት ሐሳብ አታመልጠውም፤ አንድም ቃል ከእርሱ አይሰወርም።

21 በጥበብ የሠራቸውን ድንቅ ሥራዎች አስውቧቸዋል፤ መጀመሪያም መጨረሻም የለውም፥ ምንም አይቀነስበትም፥ ምንም አይጨመርበትም፥ እርሱ የማንንም ምክር አይሻም።

22 የእጁ ሥራዎች ምንኛ ያስደስታሉ! ዓይንንስ ምንኛ ያጥበረብራሉ!

23 ሁሉም ይኖራሉ፥ ዘላለማዊ ናቸው፤ በማንኛውም ሁኔታ ትእዛዙን ይፈጽማሉ።

24 ሁሉም ጥንድና ተቃራኒ ናቸው፤ ጐደሎ አድርጐ የፈጠረው የለም።

25 አንድ ነገር የሌላውን ከፍተኛ ችሎታ ያሟላል፤ ወደ ክብሩ አተኩሮ ተመልክቶስ ማን ታከተ?

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos