“አይደለም፥ ጌታዬ፥ ቀርበህ ስማኝ፤ እርሻውን፥ በውስጡም ያለውን ዋሻውን ሰጥቼሃለሁ፤ በወገኔ ልጆች ፊት ሰጥቼሃለሁ፤ ሬሳህን ቅበር።”
ሩት 4:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቦዔዝም ሽማግሌዎችንና ሕዝቡን ሁሉ፦ ለአቤሜሌክና ለኬሌዎን ለመሐሎንም የነበረውን ሁሉ ከኑኃሚን እጅ እንደ ገዛሁ እናንተ ዛሬ ምስክሮች ናችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቦዔዝም ለሽማግሌዎቹና ለሕዝቡ ሁሉ እንዲህ አለ፤ “የአሊሜሌክን፣ የኬሌዎንንና የመሐሎንን ንብረት በሙሉ ከኑኃሚን ላይ ለመግዛቴ፣ በዛሬው ዕለት እናንተ ምስክሮች ናችሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቦዔዝም ሽማግሌዎችንና ሕዝቡን ሁሉ፦ “ለኤሊሜሌክና ለኬሌዎን ለመሐሎንም የነበረውን ሁሉ ከናዖሚን እጅ እንደ ገዛሁ እናንተ ዛሬ ምስክሮች ናችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ቦዔዝ ለሽማግሌዎቹና እዚያ ለነበሩት ሁሉ እንዲህ አለ፦ “እነሆ! የአቤሜሌክንና የልጆቹን የኬሊዎንና የማሕሎንን ንብረት ሁሉ ዛሬ ከናዖሚ በውርስ እንዳስቀረሁት እናንተ ሁላችሁ ምስክሮች ናችሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቦዔዝም ሽማግሌዎችንና ሕዝቡን ሁሉ “ለአቤሜሌክና ለኬሌዎን ለመሐሎንም የነበረውን ሁሉ ከኑኃሚን እጅ እንደ ገዛሁ እናንተ ዛሬ ምስክሮች ናችሁ። |
“አይደለም፥ ጌታዬ፥ ቀርበህ ስማኝ፤ እርሻውን፥ በውስጡም ያለውን ዋሻውን ሰጥቼሃለሁ፤ በወገኔ ልጆች ፊት ሰጥቼሃለሁ፤ ሬሳህን ቅበር።”
የሰውዮውም ስም አቤሜሌክ፥ የሚስቱም ስም ኑኃሚን፥ የሁለቱም ልጆች ስም መሐሎንና ኬሌዎን ነበረ፥ የቤተ ልሔም ይሁዳም የኤፍራታ ሰዎች ነበሩ። ወደ ሞዓብም ምድር መጡ በዚያም ተቀመጡ።
ደግሞም የምዋቹ ስም ከወንድሞቹ መካከል ከአገሩም ደጅ እንዳይጠፋ፥ የምዋቹን ስም በርስቱ ላይ እንዳስነሣ የመሐሎንን ሚስት ሞዓባዊቱን ሩትን ሚስት ትሆነኝ ዘንድ ወሰድሁአት፣ እናንተም ዛሬ ምስክሮች ናችሁ አላቸው።