ሩት 4:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቦዔዝም፦ እርሻውን ከኑኃሚን እጅ በምትገዛበት ቀን፥ ለሞተው በርስቱ ስሙን እንድታስነሣለት ከምዋቹ ሚስት ከሞዓባዊቱ ከሩት ደግሞ ትገዛለህ አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ቦዔዝ፣ “እንግዲህ መሬቱን ከኑኃሚንና ከሞዓባዊቷ ከሩት ላይ በምትገዛበት ዕለት፣ የሟቹን ስም በርስቱ ለማስጠራት ሚስቱንም ዐብረህ መውሰድ አለብህ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቦዔዝም “መሬቱን ከናዖሚ የምትገዛ ከሆነ በውርሱ የሟቹን ስም ታስጠራ ዘንድ ባልዋ የሞተባትን ሞአባዊትዋን ሩትንም አብረህ ትወስዳለህ” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቦዔዝም “መሬቱን ከናዖሚ የምትገዛ ከሆነ በውርሱ የሟቹን ስም ታስጠራ ዘንድ ባልዋ የሞተባትን ሞአባዊትዋን ሩትንም አብረህ ትወስዳለህ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቦዔዝም “እርሻውን ከኑኃሚን እጅ በምትገዛበት ቀን፥ ለሞተው በርስቱ ስሙን እንድታስነሣለት ከምዋቹ ሚስት ከሞዓባዊቱ ከሩት ደግሞ ትገዛለህ፤” አለ። |
እነርሱም እንዲህ ብለው ጠየቁት፥ “መምህር ሆይ፥ ሙሴ፦ ‘ወንድሙ ልጅ ሳይወልድ ሚስቱን ትቶ የሞተበት ሰው ቢኖር ወንድሙ ሚስቱን አግብቶ ለወንድሙ ዘር ይተካ’ ሲል ጽፎልናል።
ያም ሰው የወንድሙን ሚስት ማግባት ባይወድድ፥ ዋርሳዪቱ በበሩ አደባባይ ወደሚቀመጡ ሽማግሌዎች ሄዳ፦ ‘ዋርሳዬ በእስራኤል ዘንድ ለወንድሙ ስም ማቆም እንቢ አለ፤ ከእኔም ጋር ሊኖር አልወደደም’ ትበላቸው።