“አባትህንና እናትህን አክብር፤ መልካም እንዲሆንልህ፥ እግዚአብሔር አምላክህ በሚሰጥህ ምድርም ዕድሜህ እንዲረዝም።
ሩት 3:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ አውድማውም ወረደች፥ አማትዋም ያዘዘቻትን ሁሉ አደረገች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ተነሥታ ወደ ዐውድማው ወረደች፤ ዐማቷ አድርጊ ያለቻትንም ሁሉ አደረገች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ወደ አውድማው ወረደች፥ አማትዋም ያዘዘቻትን ሁሉ አደረገች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ሩት ወደ አውድማው ሄዳ ልክ ዐማትዋ እንደ ነገረቻት አደረገች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ አውድማውም ወረደች፤ አማትዋም ያዘዘቻትን ሁሉ አደረገች። |
“አባትህንና እናትህን አክብር፤ መልካም እንዲሆንልህ፥ እግዚአብሔር አምላክህ በሚሰጥህ ምድርም ዕድሜህ እንዲረዝም።