ሩት 3:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም፦ የለበስሽውን ኩታ አምጥተሽ ያዢው አላት፣ በያዘችም ጊዜ ስድስት መስፈሪያ ገብስ ሰፈረላት አሸከማትም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም፣ “በላይሽ የደረብሽውን ልብስ አቅርቢልኝ፤ ዘርግተሽም ያዢው” አላት፤ ዘርግታ እንደ ያዘችም ስድስት መስፈሪያ ገብስ ሰፍሮ አሸከማት፤ ከዚያም ወደ ከተማ ተመለሰች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም፦ “የለበስሽውን ልብስ አምጥተሽ ያዥው” አላት፤ በያዘችም ጊዜ ወደ ኻያ ኪሎ የሚጠጋ ገብስ ሰፍሮላት አሸከማት። እርሱም ወደ ከተማይቱ ሄደ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቦዔዝም “ሸማሽን ከላይሽ አንሺና ወደዚህ ዘርጊው” አላት። እርስዋም ሸማዋን ዘረጋች፤ ቦዔዝም ወደ ኻያ ኪሎ የሚጠጋ ገብስ ሰፈረላትና አንሥቶ በትከሻዋ አሸከማት። ከዚያም እርሱ ወደ ከተማ ሄደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም “የለበስሽውን ኩታ አምጥተሽ ያዢው፤” አላት፤ በያዘችም ጊዜ ስድስት መስፈሪያ ገብስ ሰፈረላት፤ አሸከማትም። |
እርሱም ወደ ከተማይቱ ሄደ። ወደ አማትዋም መጣች፥ አማትዋም፦ ልጄ ሆይ እንዴት ነሽ? አለቻት፣ እርስዋም ሰውዮው ያደረገላትን ሁሉ ነገረቻት።