Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሩት 3:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ቦዔዝም “ሸማሽን ከላይሽ አንሺና ወደዚህ ዘርጊው” አላት። እርስዋም ሸማዋን ዘረጋች፤ ቦዔዝም ወደ ኻያ ኪሎ የሚጠጋ ገብስ ሰፈረላትና አንሥቶ በትከሻዋ አሸከማት። ከዚያም እርሱ ወደ ከተማ ሄደ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 እንዲሁም፣ “በላይሽ የደረብሽውን ልብስ አቅርቢልኝ፤ ዘርግተሽም ያዢው” አላት፤ ዘርግታ እንደ ያዘችም ስድስት መስፈሪያ ገብስ ሰፍሮ አሸከማት፤ ከዚያም ወደ ከተማ ተመለሰች።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 እርሱም፦ “የለበስሽውን ልብስ አምጥተሽ ያዥው” አላት፤ በያዘችም ጊዜ ወደ ኻያ ኪሎ የሚጠጋ ገብስ ሰፍሮላት አሸከማት። እርሱም ወደ ከተማይቱ ሄደ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 እርሱም፦ የለበስሽውን ኩታ አምጥተሽ ያዢው አላት፣ በያዘችም ጊዜ ስድስት መስፈሪያ ገብስ ሰፈረላት አሸከማትም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 እርሱም “የለበስሽውን ኩታ አምጥተሽ ያዢው፤” አላት፤ በያዘችም ጊዜ ስድስት መስፈሪያ ገብስ ሰፈረላት፤ አሸከማትም።

Ver Capítulo Copiar




ሩት 3:15
5 Referencias Cruzadas  

ምቹ ጊዜ ካገኘን ለሰዎች ሁሉ ይልቁንም ለሚያምኑ ቤተ ሰዎች መልካም ነገርን እናድርግ።


ጨዋ ሰው ግን የጨዋነት ሥራውን በታማኝነት ያቅዳል፤ በጨዋነቱም ጸንቶ ይኖራል።


ስለዚህ ሩት በቦዔዝ እግር አጠገብ ተኛች፤ ነገር ግን ቦዔዝ ወደ ዐውድማው እንደ መጣች ማንም እንዲያውቅ ስላልፈለገ ማንም ሊያያት በማይችልበት ሰዓት በማለዳ ከመኝታዋ ተነሣች።


ወደ ዐማትዋም በመጣች ጊዜ ዐማትዋ “ልጄ ሆይ! ያ ጉዳይ እንዴት ሆነልሽ?” አለቻት። ሩትም ቦዔዝ ያደረገላትን ሁሉ ነገረቻት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios