ነገር ግን በጎ ነገር በተደረገልህ ጊዜ እኔን ዐስበኝ፤ ምሕረትንም አድርግልኝ፤ ስለ እኔም ለፈርዖን አሳስበህ ከዚህ እስር ቤት አውጣኝ፤
ሩት 3:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አማትዋም ኑኃሚን አለቻት፦ ልጄ ሆይ፥ መልካም እንዲሆንልሽ ዕረፍት አልፈልግልሽምን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህ በኋላ ዐማቷ ኑኃሚን ሩትን እንዲህ አለቻት፤ “ልጄ ሆይ፤ የሚመችሽን ቤት እንድፈልግልሽ አይገባኝምን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አማቷም ናዖሚ አለቻት፦ “ልጄ ሆይ! መልካም ይሆንልሽ ዘንድ የተመቻቸ ኑሮ የምትኖሪበትን ሁናቴ ልፈልግልሽ ይገባል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አማትዋ ናዖሚ ሩትን እንዲህ አለቻት፦ “ልጄ ሆይ! መልካም ይሆንልሽ ዘንድ የተመቻቸ ኑሮ የምትኖሪበትን ሁናቴ ልፈልግልሽ ይገባል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አማትዋም ኑኃሚን አለቻት “ልጄ ሆይ! መልካም እንዲሆንልሽ ዕረፍት አልፈልግልሽምን? |
ነገር ግን በጎ ነገር በተደረገልህ ጊዜ እኔን ዐስበኝ፤ ምሕረትንም አድርግልኝ፤ ስለ እኔም ለፈርዖን አሳስበህ ከዚህ እስር ቤት አውጣኝ፤
በሸመገለ ጊዜ ስለ ድንግልናው እንደሚያፍር የሚያስብ ሰው ቢኖር እንዲህ ሊሆን ይገባል፤ የወደደውን ያድርግ፤ ቢያገባም ኀጢአት የለበትም።
ለእናንተ፥ ከእናንተም በኋላ ለልጆቻችሁ መልካም ይሆን ዘንድ፥ አምላካችሁ እግዚአብሔር ለዘለዓለም በሚሰጣችሁ ምድር ዕድሜአችሁ ይረዝም ዘንድ፥ እኔ ዛሬ የማዝዛችሁን ሥርዐቱንና ትእዛዙን ጠብቁ።”
እንግዲህ ቆነጃጅት ሊያገቡ፥ ልጆችንም ሊወልዱ፥ ቤቶቻቸውንም ሊያስተዳድሩ፥ ተቃዋሚውም የሚሳደብበትን አንድን ምክንያት ስንኳ እንዳይሰጡ እፈቅዳለሁ፤