ሩት 2:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሩትም የገብሱና የስንዴው መከር እስኪጨረስ ድረስ ልትቃርም የቦዔዝን ገረዶች ተጠጋች፣ በአማትዋም ዘንድ ትቀመጥ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ የገብሱና የስንዴው አዝመራ ተሰብስቦ እስኪያበቃ ድረስ፣ ሩት የቦዔዝን ሴቶች ሠራተኞች ተጠግታ ቃረመች፤ ከዐማቷም ጋራ ኖረች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሩትም የገብሱና የስንዴው መከር እስኪጨረስ ድረስ ልትቃርም የቦዔዝ ሠራተኞች አጠገብ እየቃረመች ቈየች፥ ከአማቷም ሳትለይ አብራ ተቀመጠች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ሩት የገብሱና የስንዴው መከር ተሰብስቦ እስኪያበቃ ድረስ በቦዔዝ ገረዶች አጠገብ እየቃረመች ቈየች፤ ከዐማትዋም ሳትለይ አብራ ተቀመጠች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሩትም የገብሱና የስንዴው መከር እስኪጨረስ ድረስ ልትቃርም የቦዔዝን ገረዶች ተጠጋች፤ በአማትዋም ዘንድ ትቀመጥ ነበር። |