ምናሔምም ብሩን ለአሶር ንጉሥ ይሰጥ ዘንድ በእስራኤል ባለጠጎች ሁሉ ላይ በእያንዳንዱ ላይ አምሳ ሰቅል ብር አስገብሮ አወጣ። የአሶርም ንጉሥ ተመለሰ፤ በሀገሪቱም አልተቀመጠም።
ሩት 2:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለኑኃሚንም ባል የሚዛመደው ከአቤሜሌክ ወገን የሆነ ኃያል ሰው ስሙ ቦዔዝ የተባለ ሰው ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኑኃሚን፣ ከአሊሜሌክ ጐሣ የሆነ ቦዔዝ የሚባል ባለጠጋ የባል ዘመድ ነበራት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለናዖሚም በባልዋ የሚዛመዳት ሰው ከኤሊሜሌክ ወገን የሆነ ስሙ ቦዔዝ የተባለ ኃያል ሰው ነበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለናዖሚም ሀብታምና ታዋቂ የሆነ ቦዔዝ የሚባል የባልዋ የአቤሜሌክ የቅርብ ዘመድ ነበራት፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለኑኃሚንም ባል የሚዘመደው ከአቤሜሌክ ወገን የሆነ ኃያል ሰው ስሙ ቦዔዝ የተባለ ሰው ነበረ። |
ምናሔምም ብሩን ለአሶር ንጉሥ ይሰጥ ዘንድ በእስራኤል ባለጠጎች ሁሉ ላይ በእያንዳንዱ ላይ አምሳ ሰቅል ብር አስገብሮ አወጣ። የአሶርም ንጉሥ ተመለሰ፤ በሀገሪቱም አልተቀመጠም።
ከብቶቹም፦ ሰባት ሺህ በጎች፥ ሦስት ሺህ ግመሎች፥ አምስት መቶም ጥማድ በሬ፥ አምስት መቶም እንስት አህዮች ነበሩ፤ እጅግ ብዙም አገልጋዮች ነበሩት፤ ሥራውም በምድር ላይ ታላቅ ነበረ፤ ያም ሰው በምሥራቅ ካሉ ሰዎች ሁሉ ይልቅ ገናና ነበረ።
የሰውዮውም ስም አቤሜሌክ፥ የሚስቱም ስም ኑኃሚን፥ የሁለቱም ልጆች ስም መሐሎንና ኬሌዎን ነበረ፥ የቤተ ልሔም ይሁዳም የኤፍራታ ሰዎች ነበሩ። ወደ ሞዓብም ምድር መጡ በዚያም ተቀመጡ።
ሞዓባዊቱም ሩት ኑኃሚንን፦ በፊቱ ሞገስ የማገኘውን ተከትዬ እህል እንድቃርም ወደ እርሻ ልሂድ አለቻት። እርስዋም፦ ልጄ ሆይ፥ ሂጂ አለቻት።