ነገር ግን በአዳም ኀጢአት ምክንያት ከአዳም እስከ ሙሴ የበደሉትንም ያልበደሉትንም ሞት ገዛቸው፤ ሁሉ በአዳም አምሳል ተፈጥሮአልና፥ አዳምም ይመጣ ዘንድ ላለው ለእርሱ አምሳሉ ነውና።
ሮሜ 6:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ እንደ ተነሣ፥ ዳግመኛም እንደማይሞት፥ እንግዲህ ወዲህም ሞት እንደማይገዛው እናውቃለን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክርስቶስ ከሙታን ተነሥቷልና፣ ዳግመኛ እንደማይሞት እናውቃለን፤ ሞት ከእንግዲህ በርሱ ላይ ጕልበት አይኖረውም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ክርስቶስ ከሙታን ተነሥቷል፥ ዳግመኛም እንደማይሞት እናውቃለንና፤ ሞት ከእንግዲህ እርሱን አይገዛውም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ክርስቶስ ከሞት በመነሣቱ ምክንያት ዳግመኛ እንደማይሞትና ሞትም በእርሱ ላይ ሥልጣን እንደሌለው እናውቃለን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ክርስቶስ ከሙታን ተነሥቶ ወደ ፊት እንዳይሞት ሞትም ወደ ፊት እንዳይገዛው እናውቃለንና። |
ነገር ግን በአዳም ኀጢአት ምክንያት ከአዳም እስከ ሙሴ የበደሉትንም ያልበደሉትንም ሞት ገዛቸው፤ ሁሉ በአዳም አምሳል ተፈጥሮአልና፥ አዳምም ይመጣ ዘንድ ላለው ለእርሱ አምሳሉ ነውና።
በሞቱም እንመስለው ዘንድ ከእርሱ ጋር በጥምቀት ተቀበርን፤ እርሱ ክርስቶስ በአባቱ ጌትነት ከሙታን እንደ ተነሣ እኛም እንደ እርሱ በሐዲስ ሕይወት እንኖራለን።
ዘወትር በእርሱ በኩል ወደ እግዚአብሔር የሚቀርቡትን ሊያድናቸው ይቻለዋል፤ ለዘለዓለምም ሕያው ነውና ያስታርቃቸዋል።