ሮሜ 5:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኦሪት እስከ መጣች ድረስ ኀጢአት ምን እንደ ሆነች ሳትታወቅ በዓለም ውስጥ ነበረች፤ ነገር ግን የኦሪት ሕግ ገና ስላልመጣ ኀጢአት ተብላ አትቈጠርም ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕግ ከመሰጠቱ በፊት ኀጢአት በዓለም ላይ ነበር፤ ነገር ግን ሕግ በሌለበት ኀጢአት አይቈጠርም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕግ ከመሰጠቱ በፊት ኃጢአት በዓለም ነበረና፤ ነገር ግን ሕግ በሌለበት ኃጢአት አይቆጠርም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሙሴ ሕግ ከመሰጠቱ በፊት ኃጢአት በዓለም ነበር፤ ይሁን እንጂ ሕግ በሌለበት ኃጢአት ራሱ እንደ ኃጢአት አይቈጠርም ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሕግ እስከ መጣ ድረስ ኃጢአት በዓለም ነበረና ነገር ግን ሕግ በሌለበት ጊዜ ኃጢአት አይቍኦጠርም፤ |
እግዚአብሔር አምላክም መልካሙን መዓዛ አሸተተ፤ እግዚአብሔርም በልቡ አለ፥ “ምድርን ዳግመኛ ስለ ሰዎች ሥራ አልረግምም፤ በሰው ልብ ከታናሽነቱ ጀምሮ ክፋት ሁል ጊዜ ይኖራል፤ ደግሞም ከዚህ ቀደም እንዳደረግሁት ሕያዋንን ሁሉ እንደገና አልመታም።